የአርባ ምንጭ ከተማ ፋይናንስ መምሪያ ለአ/ም/ ከ/ማዘ/ቤታ/አገልግሎት ለሮድ ፈንድ ግንባታ ስራ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
የግንባታ ጨረታ ጥሪ
የአርባ ምንጭ ከተማ ፋይናንስ መምሪያ ለአ/ም/ ከ/ማዘ/ቤታ/አገልግሎት ለሮድ ፈንድ ግንባታ ስራ፡-
1. Lot-1 የጎርፍ መውረጃ ቦይ/ዲች ጥገና ሥራ
2. Lot-2 የጎርፍ መውረጃ ቦይ/ዲች ጥገና ሥራ እና ሃረድ ከቭር ጥገና
3 Lot-3 ኮብል ስቶን መንገድ ጥገና
4. Lot -4 ሰሌክት ግዥ በደረጃ ከLot-1 እስከ Lot-3 ድረስ ባለው ስራ በደረጃ 8 እና ለተደራጁ ማህበራት እና Lot-4 አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል፡፡
1. በዘርፍ ህጋዊ ንግድ ፊታድ ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
2. የግብር ከፋይ ቁጥር (TIN No) ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
3. የአቅራቢነት ምስከር ወረቀት ማስረጃ /አላይን /online/ ማቅረብ የሚችል ፡፡
4. በግንባታውን ዘርፍ መልካም የሥራ አፈፃፀም ያለው/ላት፡፡
5. ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ለእያንዳንዱ ጨረታ 10,000.00 /አስር ሺ ብር/ በባንክ የጨረታ ማስከበሪያ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
6. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ለ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በአ/ም /ከ/ፋ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር
3 በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር / በመከፈል እንድትገዙ እንገልፃለን ፡፡
7. ዋጋቸውን በማያሻማ መልኩ እንድታቀርቡ እናሳውቃለን ፡፡
8. የጨረታ ሠነድ የሚገባው ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ዕለቱ ቅዳሜ/እህድ ወይም በዓል ከሆነ በቀጣይ ቀናት ይሆናል፡፡
9. የጨረታ ሣጥን የሚታሸገው በዕለቱ ከረፋዱ 4፡00 ሲሆን የሚከፈተው 4፡30 በከተማው ፋይናንስ መምሪያ ይሆናል፡፡
10.ውል ማስከበሪያ ማስያዝ የሚችል፡፡
11.በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
12. ተጫራቾች የውል ማስከሪያ የውሉን 10% ማስያዝ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ:-0468812389/046881 4353/046881 4619
በደቡብ ክልል በጋሞ ዞን አ/ም ከተማ ፋ/ጽ/ቤት
