ኩባንያችን ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች የኤሌክትሮ ሜካኒካል እቃዎች (ፓምፕ፣ ጄኔሬተር እና ተያያዥ እቃዎች፣ እንዲሁም ቧንቧና የቧንቧ መገጣጠሚያ ፊቲንጎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ኩባንያችን ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች የኤሌክትሮ ሜካኒካል እቃዎች (ፓምፕ፣ ጄኔሬተር እና ተያያዥ እቃዎች፣ እንዲሁም ቧንቧና የቧንቧ መገጣጠሚያ ፊቲንጎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የአቃው አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የማቅረቢያ ጊዜ |
|
ሎት 1 |
የኤሌክትሮ ሜካኒካል እቃዎች (ፓምፕ፣ ጄኔሬተር እና ተያያዥ እቃዎች) |
200,000.00 |
ጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት |
|
ሎት 2 |
ቧንቧና የቧንቧ መገጣጠሚያ ፊቲንጎች |
100,000.00 |
ከ30-45 ቀናት |
ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ አቅራቢ ድርጅት ዝርዝር
የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com ማግኘት ይችላል፡፡
የተጫራቾች መመሪያ፡-
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የTIN ሰርተፊኬት፣ በዘርፉ ለመሰማራት የተሰጣቸውን ፈቃድ እና ተያያዥነት ያላቸውን ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ቴዲ የአሸከርካሪዎች ማሰልጠኛ ጎን በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሰንጠረዥ የተመለከተውን ገንዘብ በCPO ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያወጡት ወጪ በተጫራቹ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማትሪቢያቸውን እና ቴክኒካል ሰነዳቸውን ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ለእያንዳንዱን እቃ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ በትክክል ሞልተው በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
- ይህ ጨረታ በኩባንያችን የግዥ መመሪያ ነሐሴ /2013/ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።
- ኩባንያው በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው መጠን 20% ቢጨምር ወይም ቢቀንስ የጨረታ አሸናፊው ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ 05 ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) በማሰራት ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
- የማቅረቢያ ጊዜ ከላይ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው መሠረት መሆን አለበት፡፡ የአቅራቢዎች ዋጋ ቢያንስ ለ90 ቀናት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ መቆየት አለበት፡፡
- ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን በሙሉ ሆነ በክፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ዕቃው ወይም አገልግሎቱ የሚቀርብበት ቦታ ባህር ዳር ከተማ የኩባንያው ጽ/ቤት መሆን አለበት፡፡
- ማሳሰቢያ፡- እንደ ኩባንያችን ፍላጎት ውድድሩ በሎት ወይም በእያንዳንዱ እቃ ነጠላ ዋጋ መሠረት ሊሆን ይችላል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 058-220-48-26 /058-320-25-48/ በፋክስ ቁጥራችን 0582204830 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር
