በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ሊያስገነባው እና ሊያሳድሰው ለፈለገው የግንባታ ስራ አማካሪ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
የምክር አገልግሎት የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አማ 001/2018 ዓ.ም
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ሊያስገነባው እና ሊያሳድሰው ለፈለገው የግንባታ ስራ አማካሪ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የሰው ሃይል በማቅረብ የሚሰሩ ደረጃቸው ከዚህ በታች በተጠቀሰው መስፈርት በማሟላት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
|
ሎት |
የስራው አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና |
ደረጃ |
የጨረታ ሰነዱ መሸጥ የሚጀመርበት ቀን |
የጨረታ ማስገቢያ ቀን |
የጨረታ መክፈቻ ቀን |
|
ሎት-1 |
የወረዳ 01 አርቴፊሻል ሜዳ |
ከተደራጁበት የዋስትና ደብዳቤ |
ልዩ አማካሪ -1 ማህበር |
በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2፡30-10፡00 ሰዓት |
በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ |
በጋዜጣው ከወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከ4፡15 ሰዓት ጀምሮ |
|
ሎት-2 |
ብሔራዊ ቤተመንግስት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት እድሳት ጂ+0 ማስፋፊያ |
ከተደራጁበት የዋስትና ደብዳቤ |
ልዩ አማካሪ -1 ማህበር |
በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት 2፡30-10፡00 ሰዓት |
በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ |
በጋዜጣው ከወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከ4፡15 ሰዓት ጀምሮ |
አማካሪዎች ድርጅቶች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-
ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ህጋዊ ዶክሜንታችሁን ዋናውንና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።
- በዘርፉ የ2017/2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገበ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
- ማንኛውም ስራ ተቋራጭ ከፌዴራል ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የምስክር ወረቀት ያላቸው እና ከአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ እና ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ተመዝግቦ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሳይዝ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናውን (original) እና የማይመለስ ቅጂ (copy) ይዞ በመቅረብ በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮ ቀርበው ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ጨረታው የሚከፈተው በ22ኛው የሥራ ቀን በእለቱ ባለቤቱና ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በጽ/ቤቱ ከሰዓት 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡15 የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ያለበት በቴክኒካል ኦርጂናል ሰነድ ውስጥ ወይም ከፖስታው ውጪ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ቴከኒካል ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ፤ ፋይናንሽያል ሰነድ አንድ ኦርጂናልና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የታሸገውን 6 ፖስታ በአንድ እናት ፖስታ የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የስራ አይነት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ የጨረታው ፋይናንሻል ሰነድ ላይ ያልተፈረመ ሆኖ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የተስተካከለ ዋጋ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ ከጨረታው ያሰርዛል፡፡
- ተጫራቾች የሥራዎችን የዋጋ ዝርዝር እና የጨረታ መወዳደሪያ ላይ ስማቸውን፤ ፊርማቸውን፤ አድራሻቸውን ማስፈር ማህተም ማድረግ ኤንቨሎፑን በማሸግ ማስታወቂያው በወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 4፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ በፊት በአራዳ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት ምንም አይነት ውል ያላቋረጡ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድን ከማስገባታቸው በፊት የተጫራቾችን መመሪያ (instruction to Bidder (TB) and Scope of Consultancy service) እንዲያነቡ ይመክራል።
- አማካሪው ድርጅት የዲዛይን ማሻሻያ፣ የግንባታ ክትትል እና የውል ማስተዳደር ስራ ይሰራል፡፡
- አማካሪ ድርጅቱ ስራውን በጥራት ለማከናወን የሚከተላቸውን መሰረታዊ ስትራቴጂዎች የሚያቀርብ፤ እነዚህም ባለመፈጸማቸው ተጠያቂ እንደሚያደርገው ማረጋገጫ የጻፈና በስራ አስኪያጅ ወይም በኃላፊው የተፈረመ ሆኖ ማህተም ያለው ሰነድ የሚያቀርብ መሆን አለበት፡፡
- አሰሪው መ/ቤት አሸናፈው ካሸነፈበት አጠቃላይ የስራ መጠን 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይቻላል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የድርጅቱ የስራ ልምድና ማንኛውም በቴክኒካል የተጠየቁት ዶክመንቶችን አሰሪ መ/ቤት ኦርጂናል ዶከመንት ከሰጠው አካል የማጣራት መብት የተጠበቀ ነው።
- ጽ/ቤቱ ባወጣው የግንባታ ጨረታዎች ከአንድ ፕሮጀክት በላይ መግዛት የሚቻል ሲሆን መጫረት የሚፈቀደው በአንድ በመረጡት ፕሮጀክት ብቻ ይሆናል፡፡
- በአራዳ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ያሉዋቸው ተቋራጮች በጨረታ መሳትፍ የሚችሉት ከ70% በላይ የፕሮጀክት አፈጻጸም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣበት በ22ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:15 ጀምሮ በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳዳር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮ ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ አራት ኪሎ በሚገኘው በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮ በግንባር በመቅረብ መረዳት ይችላሉ።
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት
