Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግንባታዎች እና የጥገና ስራዎች ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በማሟላት የሚሰሩ ማህበራትና ስራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግልጽ ጨረታ ቁጥር 06/2018

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግንባታዎች እና የጥገና ስራዎች ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በማሟላት የሚሰሩ ማህበራትና ስራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

 

ሎት

የሥራ አይነት

የጨረታው ማስከበሪያ ዋስ ትብብር

የሚጋብዘው ደረጃ (የተቋራጩ ደረጃ)

ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ የተሰጠው ጊዜ

1

Incinerator and NCD extension building

 

ከተደራጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ

 

በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ሆነው አነስተኛ ጀማሪ አነስተኛ ታዳጊ እና አነስተኛ መብቃት ላይ ያሉ ብቻ

 

30 ቀን

2

Isolation building

3

Workshop building

4

Site work Terrazzo around Toilet, cafe and  Canopy

5

Toilet Building

6

Morgue room

7

Existing building sanitary maintenance

8

Daycare room

9

Fence work

 

  1. ለስራው ንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እና በጨረታው መሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ፣ ከፌዴራል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን / የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የደረጃ እድገት ምስክር ወረቀት ያላቸው የአቅራቢነት ምዝገባ ያላቸው (supplier list) ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።
  2. የማህበር ስራ ተቋራጮች የሚወዳደሩት ውድድር በተራ ቁጥር 1 ላይ የተገለፁ ኒካል ሰነዶች ኦርጅናል 1 ሰነዶች ኮፒ 1 ፋይናንሺያል አንድ ኦርጂናል እና ፋይናንሺያል ኮፒ 1 ለየብቻ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም፣ ፊርማ እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀ ስም እና ሎት በመጻፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል በተጨማሪም የታሸገውን 4 ፖስታ የፋይናንሻል ሰነድ በድጋሚ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም ፊርማ እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ስም እና ሎት በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይንም ሙሉ በሙሉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል።
  3. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር (10) የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ ዘወትር በስራ ሰአት ከጠዋቱ 230 እስከ 1030 ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጡሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ከግዥ ክፍል ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናው (Original) እና የማይመለስ ቅጂ (copy) ይዞ በመቅረብ እና የጨረታ ሰነዱን በነፃ መውሰድ ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው የስራ ቀን ጠዋት 400 ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ እለት 430 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
  5. ተጫራቾች ከአንድ ሎት በላይ መወዳደር ከጨረታ ተወዳዳሪነት ያሰረዛል።
  6. አሰሪ መስሪያ ቤቱ ወቅታዊ የገበያ ዋጋን ላላገናዘበ በስራ ዝርዝር ማለትም ከገበያ ዋጋ የተጋነነ ነጠላ ዋጋ (Unit Rate) (በከፍታ ወይም በዝቅታ) ተሞልቶ ካገኘ ሥራ ተቋራጮች (Cost Break down) ሰርተው እንዲያቀርቡ ያስገድዳል።
  7. አሰሪ መስሪያ ቤቱ በዋጋ ላይ ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ (unsigned Rate Correction) እና በዋጋ ላይ ፍሉድ መጠቀም (to use fluid for Rate Correction) ከጨረታ ተወዳዳሪነት ያሰርዛል።
  8. በስራ ዝርዝር በሙሉም ሆነ በአንድ የስራ አይተም ላይ ዋጋ አለመሙላት (unfilled rate) ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከማስገባታቸው በፊት የተጫራቾች መመሪያን እንዲያነቡ እና የግንባታ ሳይቱን ማየት ይመከራል።
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0924 77 78 40 በሥራ ሰዓት ብቻ በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል

 

Save Tender