በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ እንዲሁም ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፤ሞባይሎች፣ የሞባይል ከፍሎች፣ የኤሌክትሮንከስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን ፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች ፣ ደረጃ ያለፉ ፌሮ ብረቶችን እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) በግልፅና በሃራጅ ባሉበት ሁኔታ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የተያዙና የተወረሱ ተሽከርካሪችንና
ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 27/2018
በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ እንዲሁም ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፤ሞባይሎች፣ የሞባይል ከፍሎች፣ የኤሌክትሮንከስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን ፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች ፣ ደረጃ ያለፉ ፌሮ ብረቶችን እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) በግልፅና በሃራጅ ባሉበት ሁኔታ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰዉ ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ተዘጋጅቶ ከሀሙስ ህዳር 25/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑ እንገልጻለን፡፡
በመሆኑም
1. በተሸከርካሪ ግልጽ ጨረታ ለመሣተፍ ማንኛውም ዕድሜው ከ8 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (C.P.O) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኢንቮሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ በማስገባት በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል፡፡
2. በዕቃ ግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (C.P.O) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኢንቮሎፕ ወይም በፖስታ በማሸማ ለጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት የሚኖርበት ሲሆን ለሃራጅ ጨረታ ደግሞ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ይዞ ማስመዝገብ ይኖርበታል፡፡
3. በጨረታው ላይ የተሸከርካሪ ወይም የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም፡፡
4. ተጫራቾች የተሸከርካሪውንና የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ህዳር 25/2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትርበስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመከፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
5. በዕቃና ተሸከርካሪ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸዉ ዕቃዎች ወይም ተሸከርካሪዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በቅ/ፅ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተዉ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
6. የዕቃ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለዕቃዎች ብር 100,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በተ.ቁ 5 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ ማስያዝ አለበት፡፡ ነገር ግን በዕቃ ሐራጅ በጨረታ ሰነድ ላይ በሚገለጹ የተወሰኑ ዕቃዎች ላይ የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) መጠን የሚወሰን መሆኑን እንገልጻለን፡፡
7. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ፡፡
|
ተ.ቁ |
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም |
የጨረታው አይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ |
የጨረታው የመዝጊያ እና ቀንና ሰዓት
|
|
1 |
ኢ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት |
የእቃ ሃራጅ |
እስከ 29/03/2018 |
30/03/2018 4:00 ሠዓት ጀምሮ ይካሄዳል፡፡ |
|
የእቃ ግልፅ |
እስከ 30/03/2018 |
01/04/2018 3:45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሠዓት ይከፈታል |
||
|
የተሸከርካሪ ግልጽ
|
እስከ 30/03/2018 |
01/04/2018 3፡45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሠዓት ይከፈታል |
የጨረታው መከፈቻ ቦታ፡-ኢ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡
8. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል፡፡
10. ከላይ በተ/ቁ 10 በተገለፁት ቀናት ዉስጥ ከፍያዉን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃዉ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
11.መ/ቤቱ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-አዲስ አበባ ቃሲቲ ጉምሩክ :- 011-470-85-03
አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀሰበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ያስበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ
የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
