በአብክመ ግብርና ቢሮ በአምስት ቦታዎች ሼድ ኔት ግንባታ ለማሰራት በግንባታ በዘርፉ የተሰማሩትን ተቋራጮችን በደረጃ GC-5/BC-5 እና ከዚያ በላይ ያላቸውን ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።
የሼድ ኔት ግንባታ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ ግብርና ቢሮ በአምስት ቦታዎች ሼድ ኔት ግንባታ ለማሰራት በግንባታ በዘርፉ የተሰማሩትን ተቋራጮችን በደረጃ GC-5/BC-5 እና ከዚያ በላይ ያላቸውን ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል። በመሆኑም፡-
ደረጃቸው GC-5/BC-5 እና ከዚያ በላይ የሆነ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፣ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ያለውና ማቅረብ የሚችል፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል በሥራና ከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተመዘገቡና የታደሰ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣ በኢፈዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የተመዘገበና የአቅራቢነት ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- የ2017 በጀት ዓመት ከግብር ነጻ መሆናቸውን እና በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ከገቢዎች የተሰጠ ሰርተፍኬት የሚያቀርብ፡፡
- በክልሉ እና በቢሯችን ውስጥ በግንባታ ሥራ ላይ ተሰማርተው የመልካም ሥራ አፈጻጸም ያላቸውና ሥራዎችን ያላስተጓጎሉ ውል ያላቋረጡ መሆን ይገባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ንብረት አስተዳደር ዋና ስራ ሂደት ዘወትር በስራ ሰዓት በመቅረብ የማይመለስ 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በመውሰድ ቴክኒካል አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ሰነድ እንዲሁም ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ የጨረታ ሰነድ እያንዳንዳቸውን በስም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ አንድ ላይ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት በ22ኛው ቀን ይሆናል፡፡
- ከአንድ ሎት በላይ የሚሳተፍ ተጫራች ለእያንዳንዱ ሎት የተለያየ ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ ማዘጋጀት የሚኖርበት ሲሆን በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚሳተፍበትን ሎት በግልጽ በመጥቀስ የተቋራጩ ማህተምና ፊርማ ማረፍ አለበት፤ የኦርጅናል ሰነድ ላይ ማንኛውም አይነት ስርዝ ድልዝ በሚታይ መልኩ በድጋሚ መጻፍ አለበት!
ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ለ21 ተከታታይ ቀን ከዋለበት በኋላ በ22ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በዚያው ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ከዚህ በታች በሰንጠረዡ በተቀመጠው መሰረት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እና ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም ለ 120 ቀን የሚቆይ በባንክ ዋስትና ሆኖ በጥሬ ገንዘብ ብቻ ዋስትና መቅረብ አይቻልም፡፡
|
ሎት |
የስራ ቦታ |
የስራው አይነት |
ጨረታ ማስከበሪያ (ብር) |
|
1 |
ቡሬ ዙርያ ውንድጊ ች/ጣቢያ |
የሼድ ኔት ግንባታ |
100,000.00 |
|
2 |
ሁለት እጁ እነሴአብያ ች/ጣቢያ |
የሼድ ኔት ግንባታ |
100,000.00 |
|
3 |
ባ/ከተማ መሸንቲ ች/ጣብያ |
የሼድ ኔት ግንባታ |
100,000.00 |
|
4 |
አርጡማ ፋርሲ ጭሪ ች/ጣቢያ |
የሸድ ኔት ግንባታ |
100,000.00 |
|
5 |
ምዕ/ደምቢያ ግራርጌ ች/ጣቢያ |
የሼድ ኔት ግንባታ |
100,000.00 |
ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር +251-0582-26-28-91 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ
