ሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለስራ አገልግሎት የሚውል የቀላልና ከባድ ተሸከርካሪዎች ባትሪ፣ ጎማና መለዋወጫ ድርጅታችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ቁጥር 01/2018
ሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለስራ አገልግሎት የሚውል የቀላልና ከባድ ተሸከርካሪዎች ባትሪ፣ ጎማና መለዋወጫ ድርጅታችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች በዘርፉ ተገቢ የሆነ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በጨረታ እንዲሳተፉ ከገቢዎች መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ አቅራቢነት የታደሰ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው፣
- ቫት የተመዘገቡ፣
- በጨረታ ለመሣተፍ እንዲችሉ ከገቢዎችና ከጉምሩክ ፍቃድ ያላቸው፣
- የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
❖ የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት ጊዜና ቦታ፡-
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሂሳብ ቁጥር 1000604259658 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ የንግድ ፍቃዳቸውን ፎቶ ኮፒ ይዘው በመቅረብ ሲዳማ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን አዲሱ ገበያ ጊዮርጊስ ቤ/ክ/አጠገብ ካለው ሲኮስኮ ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላሉ፣
❖ ጨረታው የሚከፈትበት እና ሰነዱ የሚቀርብበት ጊዜ፦
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ ከ8፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ያስገባሉ።
- በማግስቱ በ17ኛው ቀን ከጠዋቱ ከ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
❖ የጨረታ ዋስትና፡-
- ማንኛውም ተጫራች 2% በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም ከስድስት ወር ያላነሰ ጊዜ ያለው በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ቢድ ቦንድ ዋስትና ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
❖ የጨረታ ሠነድ አስተሻሸግ ሁኔታ፡-
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ፣ የልዩ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነትና የታክስ ክፍያ ማረጋገጫ ሰነዶች፣ በጨረታው ለመሳተፍ ከገቢዎች የተሰጠ ማስረጃ እና የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /Certified bank guarantee/ ከኦርጂናል የዋጋ ማቅረቢያ ጋር በአንድ ላይ በሰም ታሽገው መቅረብ አለባቸው፡፡ ፋይናንሻል ዶኩሜንት ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በሰም ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል።
- ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በሰም ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ይህንን አስተሻሸግ ዘዴ ያልተጠቀመ ተጫራች ከጨረታው ይሠረዛል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0916071539 /0911806709 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን
