በማ/ኢ/ክ/መንግስት በስልጤ ዞን የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፋ/ፅ/ቤት ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚያስፈልጉትን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግንባታዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በማ/ኢ/ክ/መንግስት በስልጤ ዞን የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፋ/ፅ/ቤት ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚያስፈልጉትን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግንባታዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
- እንስነሬተር ውሾ ሁሉአቀፍ ጤና ኬላ
- አሽ ፒት ውሾ ሁስአቀፍ ጤና ኬላ
- ቪአይፒ መፀዳጃ ቤት ሁሉአቀፍ ውሶ ጤና ኬላ
- ፕላሴንታዊት ውሾ ሁሉአቀፍ ጤና ኬላ
- ደረቅ ቆሻሻ መቀጠያ ውሾ ሁሉአቀፍ ጤና ኬላ
- ሲፕቲክ ታንክ ውሾ ሁሉአቀፍ ጤና ኬላ
- ፎፋር 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የወንዶች መጸዳጃ ቤት
- ፎፋር 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
- በተሰማሩበት ዘርፍ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና ቲን ነበር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የስራ አፈጻጸም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ የሆነ ማንኛውም ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የ3 አመት የሥራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በህጋዊ አዲተር የተረጋገጠ ሰርተፊኬት እና ትርፋማ መሆኑን መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ማንኛውም ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ የማይመለስ 150 ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከአ/ው/ወ/ፋ/ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በመውሰድና በመሙላት መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ እንዲሁም ተጫራች ድርጅቶች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ሲፒኦ ለተራ ቁጥር 1-6 ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር)፣ ለተራ ቁጥር 7-8 ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል። በመሆኑም ጨረታው የሚከፈተው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከ15ኛው ቀን በኋላ ባለው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባልተገኙበት ከቀኑ በ6፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡
በተጨማሪም ተጫራቶች ለእያንዳንዱ ሰነድ ቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ማሳሰቢያ፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልከ ቁጥር 0910154943/0917010309
በማ/ኢ/ክ/መንግስት በስልጤ ዞን የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፋ/ፅ/ቤት
