Tender Detail

Tender Details

  • Company የሆሳዕና ማረሚያ ተቋም
  • Address ሆሳዕና : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0926 200 823
  • Website
  • Deadline29 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2025-12-29 00:00:00
  • Categories Construction Works

የሆሣዕና ማረሚያ ተቋም የተቋሙን ዙሪያ አጥር ለማስገንባት የሥራ ተቋራጮችንና ማኀበራትን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡


ለአጥር ግንባታ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ሆማተ/1159/2018

የሆሣዕና ማረሚያ ተቋም የተቋሙን ዙሪያ አጥር ለማስገንባት የሥራ ተቋራጮችንና ማኀበራትን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

1. በዚሁ መሠረት -ደረጃቸው BC-9/GC-9 (የኮንስትራክሽን ማኅበራት) የሆኑ እና ከዚያ በላይ የሆነ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው/ላት፡ የዘመኑን ግብር የከፈለች የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥርያለው/ላት እንዲሁም የVAT 15% ተመዝጋቢ የሆነች የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴርምዝገባ ምስከር ወረቀት ያለው ያላት፡፡

2. ተጫራቶች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ሆሣዕና ማረሚያ ተቋም ግዥና ፋይናንስ ንብ/አስ/የሥራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ ለዚሁ ግዥ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 500/አምስት መቶ/ በመክፈል መግዛት የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤የጨረታ ማስከበሪያን በሚመለከት የብር 30,000/ሰላሳ ሺህ /ብቻ በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም ተመሳሳይ የዋስትና ሰነድ በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር እያይዘው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

3. ተጫራቶች:- አስፈላጊውን ዕቃና ሠራተኛ አቅርቦ ሥራውን የሚሰራበትን የፋይናንሻል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጅናል፤ ሁለት ፎቶግራፍ ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ/ CPO/ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21/ሃያ አንድ / ተከታታይ ቀናት ውስጥ የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ተሞልቶ ከሙሉ ሰነዶች ጋር እንዲሁም ከላይ በተራቁጥር 01 የተዘረዘሩትን ማስረጃ ኮፒዎች አዘጋጅተው ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ተጫራቾች በሚያቀርቡት የንግድና ሌሎች ኮፒ ማስረጃዎች ላይ አጠራጣሪ ነገሮች ከታየ ኦርጅናል ማስረጃዎችን አስቀርቦ የመጣራት እና የማረጋገጥ እንዲሁም ተጫራቾቾቹም ኦርጅናል ማስረጃዎችን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።ጨረታው በ22 ኛው ቀን ከቀኑ 4.00ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች /ህጋዊ/ወኪሎቻቸው እንዲሁም ከሀዲያ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ የተላኩ የመስኩ ባለሙያዎችና የመ/ቤቱ ጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት በዕለቱ በ22ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡3ዐ ሰዓት በማረሚያ ተቋሙ ግዥ ፋይ/ንብረት አስተዳደር ቢሮ ወይም ተመሳሳይ አዳራሽ የሚከፈት መሆኑን ስንገልጽ፤ ዕለቱ የበዓላት /የዕረፍት/ ቀን ከሆነ በማግስቱ በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፍል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0912052832 ወይም 0926200823 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሆሣዕና ማረሚያ ተቋም

Save Tender