የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ለ2018 በጀት ዓመት ለመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራ የሚያገለግሉ ሚዲባስ መኪና በቁርጥ ዋጋ ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች ከሚያሟሉ አከራዮች ተከራይቶ ማሠራት ይፈልጋል።
የሚዲባስ ኪራይ አገልግሎት
የቁርጥ ዋጋ ግዥ ጥሪ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ለ2018 በጀት ዓመት ለመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራ የሚያገለግሉ ሚዲባስ መኪና በቁርጥ ዋጋ ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች ከሚያሟሉ አከራዮች ተከራይቶ ማሠራት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ
|
የተሽከርካሪ ዓይነት
|
ዝቅተኛ የመጫን አቅም
|
የስሪት ዘመን እኤአ
|
ነጠላ ዋጋ.ተ.እ. ታ በቀን
|
|
1
|
የሚዲባስ ተሽከርካሪ
|
29 ሰው ሹፌሩን ጨምሮ/
|
≥2005 GC
|
4 393.00
|
- አከራይ አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ አግባብነት ያለው የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ ሰርትፍኬት ማቅረብ እና በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ ገፅ (WWW.PPA.gov.et) የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገብ ይኖርባቸዋል።
- መመዝገብ የሚችሉት አከራይ ድርጅቶች በቀን ለኪራይ አገልግሎት ለሚወዳደሩባቸው ሚዲባሶች ባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ወይም በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ /ውልና ማስረጃ የተረጋገጠ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ውክልና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አከራይ ድርጅቶች እንዳመጣጣቸው ቅደም ተከተል ፍላጎት እስከሚሟላ ድረስ ተመዝግበው በቅደም ተከተሉ መሰረት ለሥራው ይጠራሉ።
- ለኪራይ የቀረበው የሚዲባስ ዓይነት የቴከኒክ ይዘት ከላይ በተጠቀሱት መስፈርቶች መሰረት ስለመሆኑ የባለስልጣን መ/ቤቱ የመሳሪያ አቅርቦት አስተዳደርና ጥገና ዳይሬክቶሬት እያረጋገጠ ስምሪት የሚሰጥ ይሆናል።
- የነዳጅ ዋጋ በመንግሥት ውሳኔ ሲጨምር ወይም ሲቀንስ ባለስልጣን መ/ቤቱ የዋጋ ማስተካከያ በውሉ ላይ በሚገለፀው ቀመር መሰረት ማስተካከያ ያደርጋል።
- አከራዮች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ወይም በሬዲዮ ጥሪ ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ በሥራ ቀን እና ሰዓት በባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 ለምዝገባ የሚያስፈልጉትን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ይዘው በመቅረብ መመዝገብ ይኖርባቸዋል።
ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የኪራይ አገልግሎቱን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ለተጨማሪ መረጃ፡-
አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን
(ሳርቤት ፑሽኪን አደባባይ አጠገብ)
ስልክ ቁጥር፡-011-372-2825
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባስስልጣን
