ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ቁጥር: ጣበስፋ/አግ/ብግጨ/04/2018
- በሎት-1 የገልባጭ መኪና ግዥ ብዛት 6 ለ3ኛ ጊዜ የወጣ
- በሎት-2 የተለያዩ የከባድ ማሽነሪ መለዋወጫዎች /የተለያዩ ትራክተሮች/
- በሎት-3 የተለያዩ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች እና
- በሎት-4 የተለያዩ የመስኖ ዕቃዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ የ2017/18 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ/ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት በተጨማሪም ተጫራቾች የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ አግባብነት ያለው አካል ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ታህሳስ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በተራ ቁጥር 4 በተገለፀው አድራሻ ታህሳስ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000057735167 በመክፈልና የባንክ አድቫይስ በማቅረብ በተራ ቁ. 4 ከተመለከተው ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ማስረከቢያና መክፈቻ አድራሻ ቀጥሎ የተመለከተው ነው።
አዲስ አበባ ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ ተዘንአ ሆስፒታል አካባቢ
የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንጻ፡፡
ብሎክ 4 ቢሮ ቁጥር Boo8
ስልክ ቁጥር 011 5-586725
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ የጠቅላላ ዋጋውን 2% ብር በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (ጋራንቲ) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው።
- የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ነው።
ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011558-67-25 ደውሎ መጠየቅ ይችላል፡፡
ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ
