Tender Detail

Tender Details

  • Company National Election Board of Ethiopia (የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ)
  • Address ቦሌ ፍላሚንጎ ካፌ ገባ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251 115153468
  • Websitehttps://nebe.org.et/
  • Deadline25 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2025-12-25 00:00:00
  • Categories Materials , Vehicle

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ሃገራዊ ምርጫ ለማስፈፀም የመራጮች ምዝገባ እና ስልጠና የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት ለማከናወን የሚንቀሳቀሱ የጭነት ተሽከርካሪዎችን ለማጀብ አገልግሎት የሚውሉ ፒክ አፕ ተሽከርካሪዎች የኪራይ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

የእጀባ ፒክ አፕ ተሽከርካሪ ኪራይ አገልገሎት ገዥ

የጨረታ ቁጥር NEBE/NCB/08/2018

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛው ሃገራዊ ምርጫ ለማስፈፀም የመራጮች ምዝገባ እና ስልጠና የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት ለማከናወን የሚንቀሳቀሱ የጭነት ተሽከርካሪዎችን ለማጀብ አገልግሎት የሚውሉ ፒክ አፕ ተሽከርካሪዎች የኪራይ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ምድብ አንድ፡- ለመራጮች ምዝገባ የስልጠና ቁሳቁስ ስርጭት የእጀባ ፒክ አፕ ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ

ምድብ ሁለት፡- ለመራጮች ምዝገባ ቁሳቁስ ስርጭት የእጀባ ፒክ አፕ ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም

  1. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ከቦርዱ ግዥ ሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 107 ማግኘት ይችላሉ።
  2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሠርተፍኬት፣የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሠርተፍኬት እና በመንግስት ኤሌክትሮኒክስ ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ ስለመሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. የጨረታ ሰነዱን ከቦርዱ የግዥ አስተዳደር የሥራ ክፍል በመውሰድ ሞልተው አግባብ ባለው አካል በመፈረም ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ፡- ለምድብ አንድ ብር 50,000.00 (ብር ሃምሳ ሺህ 00/100) ለምድብ ሁለት ብር 100,000.00 (ብር አንድ መቶ ሺህ 00/100) በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርበታል።
  5. ተወዳዳሪዎች ቴክኒካል ፕሮፖዛል እና ፋይናንሻል ፕሮፖዛል በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  6. ጨረታው ታህሳስ 16 ቀን 2018 . ከቀኑ 800 ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 830 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
  7. ቦርዱ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

 

አድራሻችን፡- ቦሌ ፍላሚንጎ ሬስቶራንት ገባ ብሎ

ስልክ ቁጥር፡- +251 11 515 3468

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

Save Tender