Tender Detail

Tender Details

  • Company አፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ
  • Address , Phone: 0336660125
  • Website
  • Deadline21 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price1000.00
  • opening date2025-12-21 00:00:00
  • Categories Construction Works

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2018 ዓ.ም በጀት አመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውሉ ደረጃውን የጠበቀ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል።


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ 2018 . በጀት አመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውሉ ደረጃውን የጠበቀ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደስ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣባት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ሠመራ ትም/ቢሮ ቁጥር 6 የጨረታዉን ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ሀሰብ እና ዋጋ በሠም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዶችን በመለየት 2 ኮፒ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (..) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሽገ ፖስታ ትምህርት ቢሮ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትምህርት ቢሮ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 11ኛዉ ቀን 300 ሠዓት ይከፈታል።
  8. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 በስልክ ቁጥር 033-666-01-25/ በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

 

አፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ

Save Tender