Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
  • Address አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-56-98-69
  • Websitehttps://press.et/
  • Deadline27 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • opening date2025-12-27 00:00:00
  • Categories Aluminium Supply and Work

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት የአልሙኒየም እስቴጅና ኢንትራንስ ጌት እንዲሁም የአልሙኒየም ትረስ እና አሉሚኒየም ድንኳን በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 009/2018

 

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት 2018 በጀት ዓመት የአልሙኒየም እስቴጅና ኢንትራንስ ጌት እንዲሁም የአልሙኒየም ትረስ እና አሉሚኒየም ድንኳን በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም:- ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  • በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው
  • የንግድ ምዝገባ
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት
  • የቫት ሰርተፍኬት
  • በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገበ

ሎት 1. የአልሙኒየም እስቴጅና ኢንትራንስ ጌት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)

ሎት 2. የአልሙኒየም ትረስ  እና አልሙኒየም ድንኳን የጨረታ ማስከበርያ መጠን 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሲ..ኦ፣ ቢድቦንድ ወይም ለጥቃቅንና አነስተኛ ከአደራጃቸው አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ በማያያዝ ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት አንደኛ ፎቅ በሚገኘው አቅርቦት መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቴክኒካል ዶክመንት ዋና እና ቅጂ እንዲሁም የሚወዳደሩበትን ዋጋ ዋና እና ቅጂ በሚል በጉልህ በሚታይ መልኩ በመጻፍና የሚወዳደሩበትን ሎት በፖስታዎቹ ላይ በመግለጽ በአራት የተለያየ ፖስታ በማሸግ ማሰገባት የሚኖርባቸው ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ ቴክኒከ ዋና ሰነድ ፖስታ ውስጥ ተያይዞ መገኘት አለበት፡፡

  • በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 100 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  • ስርዝ ድልዝ ያለውና ያልተፈረመ እንዲሁም በጉልህ የማይታይ አጠራጣሪ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  • ጨረታው 16ኛው ቀን ከረፋዱ 400 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 430 በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ 1 ፎቅ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን የተጫራቹ አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም፡፡ የጨረታ መክፈቻው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ ባለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • ድርጅታችን አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

አድራሻ፡- አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት

 

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

 

Save Tender