Tender Detail

Tender Details

  • Company የቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል /ቂሊንጦ/
  • Address ቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር አ/አ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 4 71 63 33
  • Website
  • Deadline30 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2025-12-30 00:00:00
  • Categories Agriculture And Farming , Food And Beverage , Firewood , Merchandise

በቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ለቀጠሮ የህግ እስረኞች ለምግብ ፍጆታ አገልግሎት የሚውሉ የወጥ ጥራጥሬ እህሎች፣ የምግብና የወጥ ማጣፈጫዎች፣ አትክልቶች ጥራቱን የጠበቀ ነጭ ሰርገኛ ጤፍ፣ የበቆሎ ዱቄት፣ የፍርኖ ዱቄት እና የባህር ዛፍ የማገዶ እንጨት ለስድስት ወር ግዜ ውስጥ አጠቃሎ ለማስገባት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ለቀጠሮ የህግ እስረኞች ለምግብ ፍጆታ አገልግሎት የሚውሉ የወጥ ጥራጥሬ እህሎች፣ የምግብና የወጥ ማጣፈጫዎች፣ አትክልቶች ጥራቱን የጠበቀ ነጭ ሰርገኛ ጤፍ፣ የበቆሎ ዱቄት፣ የፍርኖ ዱቄት እና የባህር ዛፍ የማገዶ እንጨት ለስድስት ወር ግዜ ውስጥ አጠቃሎ ለማስገባት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል፡፡

በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መመሪያና መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን፣ በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው የተገለፀ መሆን አለበት፡፡
  2. የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  3. የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው::
  4. የመንግስት /ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል አቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎች ጉምሩክ ባለስልጣን የዘመኑን ግብር ከፍለው ስለማጠናቀቃቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::
  5. ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ ከአደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
  6. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ስም በአካውንት ቁጥር 1000007971347 ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 25 መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቅረቢያዎችን /ፋይናንሻል ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለበት፡፡ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ በአንድ ላይ አሽጎ ያቀረበ ተወዳዳሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ውጭ ይደረጋል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራቾች የሚያስገቡት ሰነድ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ እንዲሁም ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ በተለያዩ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የሚጫረቱበትን የጨረታ ሰነድ ቁጥር በትክክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ እና በሁሉም የመጫረቻ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም በመምታት ማስገባት ያለባቸው ሲሆን ስርዝ ድልዝ ፣በፍሉድ የጠፋ ሰነድ፣ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የለውም፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያስይዙት ሲፒኦ ከቴከኒክ ሰነዶች ከኦርጅናሉ ጋር በአንድ ላይ አሽገው ማቅረብ አለባቸው::
  10. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO በፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ሥም አዘጋጅተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ እስከ ታህሳስ 21 ቀን 2018 . ከቀኑ 430 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣ እንዲሁም የባንክ ዋስተና የሚያስይዙ ተጫራቾች የቆይታ ጊዜው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 90 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርበታል፡፡
  11. ጨረታው ታህሳስ 21 ቀን 2018 . ከቀኑ 500 ሰዓት ተጫራቾች ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቂሊንጦ በሚገኘው በመ/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  12. የጨረታው ዝርዝር መመሪያ በጨረታ ሰነዱ ተዘርዝሮ ቀርቧል፡፡
  13. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም፣ እንዲሁም ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
  14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በአጋጣሚ ምክንያት ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡

 

አድራሻ፡- ቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር / ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ

ለበለጠ መረጃ:- 0114 71 63 33/0118 88 60 89/011434 89 86 ደውለው መጠየቅ ይቻላል ::

 

የቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል /ቂሊንጦ/

 

Save Tender