መ/ቤታችን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን በሥሩ ላሉት የጥገና መንገዶች እና የመንገድ ሥራ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን እና ኢንጅነሪንግ መሣሪያዎች መገልገያ ማለትም ለጠጠር ማመላላስ አገልግሎት ገልባጭ መኪና እስከነ ሎደሩ ኪራይ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል::
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ማ/ኢ/ክ/መ/ባ/DR/118
መ/ቤታችን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን በሥሩ ላሉት የጥገና መንገዶች እና የመንገድ ሥራ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን እና ኢንጅነሪንግ መሣሪያዎች መገልገያ ማለትም ለጠጠር ማመላላስ አገልግሎት ገልባጭ መኪና እስከነ ሎደሩ ኪራይ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል::
በመሆኑም
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን በኮንስትራክሽን መሳርያዎች እና መገልገያዎች ማከራየት ሥራ የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት፣ የመንግስት መ/ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ መካፈል/መሳተፍ የሚያስችል ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት እንዲሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ኦንላይን የተመዘገቡ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቮሎፕ ፋይናንሻል ፕሮፖዛሉንና ቴክኒካል ፕሮፖዛሉን በአንድ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ “ኦርጅናል” እና “ኮፒ” በማለት እና የጨረታ ማስከበርያውን በተለየ ፖስታ ለብቻው ማቅረብ ይኖርባቸዋል ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው።
- አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ይሆናል። ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተመሳሳይ ሠዓት የሚከፈት ይሆናል ።
- ተጫራቾች ለየፕሮጀክቱ ብር 250,000.00 /ሁለት መቶ ሀምሳ ሺህ ብር/ ብቻ የጨረታ ማሰከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ c.p.0 ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበርያ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመርያ መሰረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው ከጨረታው ደንብና መመርያ ውጪ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ:: የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ግብዓት አቅርቦትና አስተዳደር ደጋፊ ሥራ ሂደት ወደ ወልቂጤ ኢንዲስትሪያል ኮሌጅ በሚወስደው አስፋልት መንገድ ላይ የድሮው የወልቂጤ ከተማ ስፖርተኞች ማደርያ ጊቢ ውስጥ እንገኛለን።
ስልክ ቁጥር +251113659932 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይቻላል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን
