Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን
  • Address አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ፒያሳ/እስታቲክስ እናት ህንጻ ፊት ለፊት ዋስትና ንግድ ማአከል 15ኛ ፎቅ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-27-68-25
  • Website
  • Deadline26 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2025-12-26 00:00:00
  • Categories Vehicles Rent

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የግዥና ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በ2018 በጀት ዓመት የመኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


 

ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 004/2018

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የግዥና ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት 2018 በጀት ዓመት የመኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

1. ሎት 1 የፒክ አፕ መኪና፣ የሚኒባስ መኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡

  1. ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤
  2. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ/የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ከገቢዎች የተወዳዳሪነት ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፣
  5. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር/ Tin No / ያላቸው፣
  6. በመንግስት ግዥና የንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ድረ-ገጽ WWW. PPA.gov.et)
  7. ተጫራቾች የሚያስዙት የጨረታ ማስከበሪያ/CPO/

. የፒክ-አፕ መኪና --------------- 20,000 ብር (ሃያ ሺህ ብር) CPO

ለ. የሚኒባስ መኪና ---------------- 20,000 ብር (ሃያ ሺህ ብር ብቻ) CPO

  1. ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ በመ/ቤታችን ስም CPO ማስያዝ አለባችሁ ነገር ግን CPO ያላስያዘ ቢኖር ከጨረታ ውጪ ይሆናል፤
  2. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመወዳደር ጨረታው ከተዘጋጀ በኋላ የሚወዳደሩበት በተሰጠው በእስፔስፍኬሽን መሰረት መቅረብ አለበት፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 7 የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ካወጣበት ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ 15 ፎቅ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በመቅረብና የማይመለስ 300 ብር /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፣
  4. አሸናፊው ድርጅት ጥራቱን ያልጠበቀ ዕቃ ወይም አገልግሎት ካቀረበ በራሱ ወጪ የመለወጥ ግዴታ አለበት፣
  5. /ቤቱ ካቀረበው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ በአማራጭነት ማቅረብ አይቻልም፤
  6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሽል ኦርጅናል እና ኮፒ ደግሞ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ ዋጋ ሞልታችሁ በተናጠል ለየብቻ በፖስታ አድርጋችሁ የድርጅታችሁን ማህተምና ፈርማ የተወዳደራችሁበትን የሎት አይነት በፖስታው ላይ እየጻፋችሁ አስገቡ ካልጻፋችሁበት ደግሞ ፖስታችሁ እንደማይከፈት እያወቃችሁ የተባለበትን በሙሉ በማድረግ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ወደ ህንጻው ስትገቡ በቀኝ በኩል ባለው ሊፍት 15 ፎቅ ፊት ለፊት ለጨረታ ተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፤
  7. ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ለምትጫረቱባቸው ዕቃዎች (አገልግሎቶች የጨረታ ሰነዱን በነፃ ለመውሰድ

. ካደራጃችሁ /ቤት ደብዳቤ ማምጣት አለባችሁ፤

ለ. ሰነዱን በነፃ ለመውሰድ በመመሪያ መሰረት ለምታቀርቡት ዕቃ (አገልግሎቶች) አምራች መሆን አለባችሁ፤

  1. ተጫራቾች /ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርባት በትክክል መሙላት አለባቸው::
  2. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ አሸናፊው ድርጅት ባሸነፈበት ዕቃ ወይም አገልግሎት ላይ ውል ሲገባ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል እንዲሁም አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ጨረታ ተከፍቶ ውጤት ከተለጠፈ 8 የሥራ ቀናት በኋላ በመቤታችን ቀርቦ ውል መግባት አለበት፡፡
  3. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ጋዜጣው ከወጣበት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 300 ሰዓት ታሽጎ 330 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 11 ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የሥራ ቀናት ውስጥ የሚከፈት ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  1. ተጫራቾች የቀረበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑንና ያላካተተ መሆኑን መገለጽ አለባችሁ፡፡ ይህ ካልሆነ ግን /ቤቱ የቀረበውን ዋጋ ቫትን እንዳካተተ አድርጎ ይወስደዋል፡፡
  2. /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

 

አድራሻ - አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ክፍለ ከተማ አራዳ ወረዳ 1 ፒያሳ/ ስታስቲክስ ጎን እናት ህንጻ ፊት ለፊት ዋስትና ንግድ ማእከል 15 ፎቅ ላይ ይገኛል ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-127-68-25 ይደውሉ፡፡

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን

 

Save Tender