በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የISVCD ፕሮጀክት የመኪና ግዥ በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በተዘረዘረው መሰረት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የመኪና ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 152/18
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የISVCD ፕሮጀክት የመኪና ግዥ በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በተዘረዘረው መሰረት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ
|
የዕቃው አይነት
|
መለኪያ
|
ብዛት
|
የጨረታ ማስከበሪያ
|
የሚታሸግበት ሰዓት
|
ሰነዱ የሚገኝበት ቦታ
|
|
1
|
35 ኩ/ል የሚጭን መኪና
|
በቁጥር
|
01
|
200,000
|
በ31ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል
|
ደ/ኢ/ግ/ቢሮ ዲላ መምህራን ኮሌጅ ግቢ
|
በንግድ ሥራ ዘርፉ የታደሰ ፍቃድ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውና የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃዎች ያላቸውና የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለ60 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል።
- በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ያስያዙበትን ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በቢሮ የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው ተከታታይ እስከ 30ኛ ቀን 11፡30 ድረስ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል በዲላ ከተማ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ መምህራን ኮሌጅ ግቢ ከሚገኘው የግብርና ቢሮ ግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ በመሙላት ይህ የጨረታ የቴክኒካልና ፋይናንሻል የማጫረቻ ሰነዶች በአንድነት ፖስታ በማዘጋጀት በ31ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት በቢሮ ግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል። እንዲሁም የጨረታው ሳጥን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች (ተወካዮቻቸው) በተገኙበት በቢሮው የግዥ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል ይከፈታል።
- ቢሮው በቀረበው ጨረታ ላይ ካሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት የግዥውን 20% ፐርሰንት መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል።
- የጨረታው ሳጥን መክፈቻ በ31ኛው ቀን የመንግሥት የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣይ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
- ሁለት ተወዳዳሪዎች ያቀረቡት ዋጋቸው እኩል በሚሆንበት ወቅት በእጣ የሚለይ ይሆናል።
- ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ 046-131 0134 ይጠቀሙ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ
