Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን
  • Address አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከግሩም ሆስፒታል ከፍ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-8-27-99-79
  • Website
  • Deadline23 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2025-12-23 00:00:00
  • Categories Construction and Water Works , Building Construction , Supply of Water

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት የቦቴ ውሃ አቅርቦት እና የመፀዳጃ ቤት አገልግሎት ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር 002/2018

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት /ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን አገልግሎት ለሚሰጣቸው /ቤቶች 2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን 2/ሁለት/ሎት ማለትም፡-

ሎት 1 - የቦቴ ውሃ አቅርቦት፣

ሎት 2- የመፀዳጃ ቤት አገልግሎት፣

ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት አሟልቶ በጨረታው መወዳደር ይችላል።

  1. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ ንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ያላቸው፣ ግብር ከፋይነት ምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት አቅራቢነት ማስረጃ ያለው፣ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ የሆነ፣
  2. በዘርፉ በገንዘብ ሚኒስቴር በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እንዲሁም 2017 በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆናቸው ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ አካል በጨረታ መሳተፍ እንዲችሉ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት /ክሊራንስ/ ማቅረብ የሚችሉ
  3. የጨረታ ማስከበሪያ፡- ለእያንዳንዱ ሎት ከአጠቃላይ ለበጀት ዓመቱ ከተበጀተው በጀት 0.5-2% የተሰላነው

ሎት 1

 

ሎት 2

 

23,900.00

 

10,000.00

 

 

  1. በእያንዳንድ ሎት ለብቻው በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ADDIS KETEMA SUB CITY ADMINSTRATOIN PUBLIC SERVICE & HUMAN RESOURCE DEVELOPMENT OFFICE PURCHASING ADMINISTRATION SUPPORTIVE PROCESS በሚል ስም የተሰራ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  2. የሚታዘዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ተቀባይነት የሚኖረው የሲፒኦ ቁጥር የሚታይ ከሆነ፣ የተጫራቹን ስም በግልፅ የሚነበብ ከሆነ ሲፒኦ ጀርባ ላይ የባንኩ ማረጋገጫ ማህተም ያለው ከሆነ ብቻ ነው።
  3. ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10/አስር/ የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር / በመከፈል የጨረታውን ሠነድ በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 230 እስከ 1130 በአ/// ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት /ቤት የፋይናንስ ቡድን 6ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 መውሰድ ይችላሉ።
  4. በክፍል 6 ባዶ በቴክኒክ መመዘኛዎች ላይ ተሟልቶ፣ ተፈርሞ እና ማህተም ተደርጎ፣ በሁሉም ገጽ ላይ ተፈርሞ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎ ሙሉ የጨረታ ሰነድ | መመሪያ/ ተመላሽ ይደረጋል።
  5. የጨረታ ሰነዱ ቴክኒካል ዋናውን አንድ/1/ እና ፎቶ ኮፒ/1/ ፋይናንሺያል ሰነድ ዋናውን አንድ/1/ እና ፎቶ ኮፒ አንድ/1/ ለየብቻ በፖስታ ታሸጎ በድምሩ አራት/4/ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ኦርጅናል/ኮፒ ቴክነካል እና ፋይናንሺያል በሚል በፖስታው ላይ በመግለጽ/በመፃፍ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ///ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት /ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን 6ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 ማስገባት ይኖርበታል።
  6. የጨረታ ሰነድ ለመግዛት እና ፖስታውን ለማስገባት ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ 10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 1130 ድረስ በአዲስ ከተማ /ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት /ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን 6 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 ማስገባት ይችላሉ፡፡ 11ኛው የስራ ቀን ጠዋቱ 300 የጨረታው ሳጥን የሚታሸግ ሲሆን በዚሁ ቀን ጠዋቱ 330 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፤ ነገር ግን 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  7. /ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ - 011-8-27-99-79 / 011-8-95-92-23 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፤

አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከግሩም ሆስፒታል ከፍ ብሎ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት /ቤት የፋይናንስ ቡድን፤ 6 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት /ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን

Save Tender