የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር አ/አ/ከ/አ/የሰ/ፀ/አስ/ቢሮ /እቃ/አገ/ግ/ጨ/003/2018ዓ/ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት1 የመኪና ጥገናና የሰርቪስ አገልግሎት
ስለሆነም ጨረታውን መካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው የዕቃ አቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ቲን እና VAT ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ፒያሳ ከሚገኘው ማዘጋጃ ቤት 2ኛ ፎቅ ከመ/ቤቱ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት 309 ቁጥር መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሚወዳደሩበት ሎት በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም የባንክ ዋስትና /unconditional bank guarantee) በመ/ቤታችን ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የኢንሹራንስ ዋስትና አንቀበልም።
ሎት1. የመኪና ጥገናና የሰርቪስ አገልግሎት ....... 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ሞልተው በመፈረም እና ህጋዊ ማህተም በማድረግ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ኦሪጅናል እና ኮፒ በየሎቱ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተራ ቁጥር 2 በተጠቀሰው አድራሻ የመ/ቤቱ ግዢ ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በ11ኛው ቀን እስከ 3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- በመ/ቤቱ ዋጋ መሙያ ያልተሞላ ዋጋ ፊርማና ማህተም የሌለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ11ኛው ቀን 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሚጫረቱበት እያንዳንዱ እቃ ጥራት በቴክኒክ ብቃታቸው ከተመረጡ በዋጋ የሚወዳደሩ ይሆናል። አማራጭ ጨረታ አይፈቀድም።
- አሸናፊው ድርጅት ባሸነፈበት ጠቅላላ እቃዎች ዋጋ 10 በመቶ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ አሸናፊነቱ ከታወቀበት ከ7ኛ ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ ውል መፈረም አለበት።
- በተራ ቁጥር 7 መሰረት ውል የማይፈጽሙ አሸናፊዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ በማድረግ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ መጠቀም ይችላል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 091575439 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ፡- ፒያሳ ከንቲባ ፅ/ቤት ጊቢ ውስጥ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 318
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ
