የደ/ብርሃን መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በመደበኛ በጀት እና በውስጥ ገቢ በጀት ከዚህ በታች የተጠቀሰውን እቃዎች መግዛት ይፈልጋል።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ብርሃን መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በመደበኛ በጀት እና በውስጥ ገቢ በጀት ከዚህ በታች የተጠቀሰውን እቃዎች መግዛት ይፈልጋል።
ሎት1. የፅህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 3. የመኪና ቅባቶች፣ ጎማና ባትሪ፣ ሎት 4. የፅዳት እቃዎች፣ ሎት5. የአርት እቃዎች፣ ሎት6.የጥገና እቃዎች /ህንፃ መሳሪያ እና የቧንቧ እቃዎች/
በዚህም መሠረት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በግዥው ላይ እንድትሣተፉ ይጋብዛል፡፡
- በመስኩ ንግድ ፈቃድ ያለው እና ከብር 200.000.00 /ሁለት መቶ ሺህ/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ኮፒ ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
- ከላይ የተጠቀሡትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶች ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ፡-
|
ተ.ቁ |
የግዥው ዓይነት /የእቃው ዝርዝር/ |
የሚያሲዙት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን |
|
ሎት1 |
የፅህፈት መሳሪያ |
25,000.00 |
|
ሎት2 |
ኤሌክትሮኒክስ |
10,000.00 |
|
ሎት3 |
የመኪና እቃዎች |
25,000.00 |
|
ሎት4 |
የፅዳት እቃዎች |
5,000.00 |
|
ሎት5 |
የአርት እቃዎች |
5,000.00 |
|
ሎት6 |
የጥገና እቃዎች /ህንፃ መሳረያ እና የቧንቧ እቃዎች |
15,000.00 |
- በባንክ በተመሠረት የክፍያ ትእዛዝ /CPO ወይንም ሁኔታ ላይ ያልተመሠረት የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 013/12 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሸጐ በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት ታሽጎ በተመሣሣይ ሠዓት ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የመንግስትን ጥቅም ባልጠበቅ መልኩ በጥቅል/በነጠላ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በሎት የቀረቡ እቃዎች ላይ ዋጋ መስጠት ግዴታ ነው፡፡ ሁሉንም እቃዎች ላይ ዋጋ ያልሞላ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- መስራቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ተወዳድረው አሸናፊ የሆነው ድርጅት የእቃ ርክክቡ ቦታ ደ/ብረሃን መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ግቢ ንብረት ክፍል ይሆናል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011681 44 89 /01681013/4 መጠየቅ ይችላል፡፡
የደ/ብርሃን መምህራን ትምህርት ኮሌጅ
