Tender Detail

Tender Details

  • Company Habesha Cement Share Company (ሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ.)
  • Address አሮጌው ቄራ ከንግድ ማተሚያ ቤት ጀርባ ጌት-አስ ኢንተርናሽናል ሕንፃ 7ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0944122311
  • Websitehttps://habeshacement.com/
  • Deadline25 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price
  • opening date2025-12-25 00:00:00
  • Categories Safety And Security , Personal Protective Safety Equipment , Safety Clothe And Shoes

ድርጅታችን ሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር የተለያዩ የደህንነት መጠበቂያ መገልገያዎችን ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


 

ሐበሻ ሲሚንቶ

HABESHA CEMENT

 

የተለያዩ የደህንነት መጠበቂያ መገልገያዎችን ለመግዛት የወጣ ጨረታ

Procurement Ref. No. HCSC/EHS/002/2018

 

ድርጅታችን ሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር የተለያዩ የደህንነት መጠበቂያ መገልገያዎችን ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሟያሟሉ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በፖስታ አሽገው ግዢ እና አቅርቦት ክፍል እስከ ታኅሣሥ 16 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በዕለቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እያሳወቅን፤ ተወዳዳሪዎች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ከላይ እስከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ድረስ ብቻ ከታች በተመለከተው አድራሻ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን

  1. ማንኛውም ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈለ ድርጅት በጨረታው መወዳደር የሚችል ሲሆን ተጫራቾች የፈቃዳቸውን ኮፒ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆቸው ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ዋጋ የሚያቀርቡባቸውን እቃዎች መጥቀስ/ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ዋጋ ያቀረቡበትን የዕቃ አይነት በግልጽ መጻፍ ይኖርባቸዋል
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 (መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይንም የባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
  4. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶችም ሆኑ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የሚደረጉ የማሻሻያ ጥያቄዎች ተቀባይነት የላቸውም
  5. አሸናፊ ሆኖ የተመረጠ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ውል በመግባት 5 ባልበለጡ የስራ ቀናት ውስጥ ዕቃዎቹን ማቅረብ ይጠበቅበታል
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከቫት ወይም ከማንኛውም የመንግስት ታክስ በፊት እንዲሁም ታክስን ጨምሮ መሆኑን በግልፅ ማመልከት ይኖርበታልይህ ባልሆነበት እና ዋጋ በግልፅ የማያቀርቡ ተጫራቾች ከጨረታው ሊሰረዙ ይችላሉ ስርዝ ድልዝ የዋጋ ማቅረቢያ ተቀባይነት አይኖረውም
  7. ሐበሻ ሲሚንቶ . ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን በተጨማሪም ለግዥ የቀረቡትን አቃዎች ዝርዝር ብዛት የመጨመርም የመቀነስም መብቱ የተጠበቀ ነው
  8. ተጫራቾች ለግዥ የቀረቡትን የደህንነት መጠበቂያ እቃዎች ዝርዝር እንዲሁም ተጨማሪ መረጃዎችን ከዚህ በታች በተቀመጠው የድርጅቱ አድራሻ ማግኘት ይችላሉ

 

አድራሻ፡ አሮጌው ቄራ ከንግድ ማተሚያ ቤት ጀርባ ጌት-አስ ኢንተርናሽናል ሕንፃ 7 ፎቅ

ስልክ: 0944122311/0912850906

 

ሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ

Save Tender