ሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በ2018 በጀት ዓመት ለሥራ የሚፈልጋቸውን የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና ካሜራ አክሰሰሮች እና Server በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በ2018 በጀት ዓመት ለሥራ የሚፈልጋቸውን
- ሎት 1. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና ካሜራ አክሰሰሮች
- ሎት 2 Server በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በዚህ ጨረታ መወዳደር የሚችሉ
- ህጋዊ የንግድ ምዝገባ ፍቃድ ያላቸው
- በመስኩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው
- የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ያላቸው
- በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ያላቸው ድርጅቶች ሀዋሳ ወንዶ ንግድ ኩባንያ ህንጻ ጀርባ በሚገኘው በኮርፖሬሽኑ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 በአካል መምጣት የተዘጋጀውን ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 5,000 ብር በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም ቢድ ቦንድ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታውን የመወዳደሪያ ዋጋ ኮርፖሬሽኑ ባዘጋጀው ሰነድ ላይ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ሥራ ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ፖስታዎችን ቴክኒካል ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ እያንዳንዳቸውን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ ለዚህ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታውም በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የዕረፍት ቀን ወይም የበዓል ቀን ሲሆን በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፍልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0916037261/ 0462121480 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን
