የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩከ ቅ/ፅ/ቤት በ11/04/2018 ዓ/ም በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2018 የበጀት ዓመት
- የተለያዩ የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦች
- የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች
- የተለያዩ የፅዳት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላላችሁ።
- የ2017/18 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ በዘርፉ ያላችሁ፡፡
- ተጫራቾች የተጨመረ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆን መረጃ ማቅረብ የሚችል።
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባችሁን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ ግዥ መ/ቤት ድረስ በራሱ ወጪ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ኮፒና ኦሪጅናል ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማሸግ አለባቸው።
- ሰርዝ ድልዝ ያለው ፤ የማይታይ የጨረታ ሰነድ ወይም የዋጋ ዝርዝር ተቀባይነት የለውም።
- ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ የውል ማስከበሪያ የአሸነፉበትን ዋጋ 10% ማስያዝ የሚችል።
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኮሌጁ ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ክፍል ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ጨረታ ለየብቻ 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ አለባቸው።
- የተለያዩ የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦች ጨረታው የሚከፈተው 21/04/2018 ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች ጨረታው የሚከፈተው በ21/04/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የተለያዩ የፅዳት እቃዎች ጨረታው የሚከፈተው በ22/04/2018 ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚሞሉትን ዋጋ በመስሪያ ቤቱ ሰነድ ብቻ ላይ መሆን አለበት።
- የጨረታው ማስከበሪያ
- ለሶስቱም ጨረታዎች ለየብቻ 20,000 (ሃያ ሺ ብር) በCBE, CBO እና Sinqe ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022 812 3956 ደውለው መረዳት ይችላሉ።
አዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ
