የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለ2018 በጀት ዓመት በግብርና ግብዓት እና ገጠር ፋይናንስ አቅርቦት ዘርፍ በኩል በዳውሮ ዞን ተርጫ ዙሪያ ወረዳ ጎርቃ በሪሳ ቀበሌ የኖራ ድንጋይ መፍጫ ማሽን ማቅረብና መትከል፣ የመትከያ ሼድ፣ የጥበቃ ቤት እና የመፀዳጃ ቤት ግንባታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ ግብርና ቢሮ የጨረታ ቁጥር 02
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለ2018 በጀት ዓመት በግብርና ግብዓት እና ገጠር ፋይናንስ አቅርቦት ዘርፍ በኩል በዳውሮ ዞን ተርጫ ዙሪያ ወረዳ ጎርቃ በሪሳ ቀበሌ የኖራ ድንጋይ መፍጫ ማሽን ማቅረብና መትከል፣ የመትከያ ሼድ፣ የጥበቃ ቤት እና የመፀዳጃ ቤት ግንባታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶችን የማሟላት ግደታ አለባቸው።
1ኛ. ተጫራቾች የ2018 በጀት ዓመት በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2ኛ. የንግድ ስራ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የመሰረት ልማት ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይነት መለያ (TIN-NO) ማስረጃና የንግድ ስራ ፍቃድ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3ኛ. የተጫራቾች ደረጃ Eectromechanical /BC3/GC3/ እና ከዚያ በላይ መሆናቸውን የሚገልፅ ህጋዊ ማስረጃ ኮፒ ማስያዝ የሚችሉ።
4ኛ. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ ስም በተከፈተው አካውንት ቁጥር 1000454620918 ገቢ በማድረግ አድቫይስ በመያዝ ከግዥ/ክ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 4 ዘወትር በስራ ሰዓት ለተከታታይ 30 ቀናት መውሰድ ይቻላል።
5ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 900,000.00 (ዘጠኝ መቶ ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ (CPO)፣ በማይሻር ሌተር ኦፍ ክሬዲት (L/C) እና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /Unconditional bank guarantee / በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ከልል መንግስት ግብርና ቢሮ ስም በማስያዝ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6ኛ. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ /Technical and Financial/ ዶክመን አንድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ሁለት ኮፒ በተለያየ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 30ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ውሰጥ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ በግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 4 ለዝሁ ተግባር በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7ኛ, ጨረታው በወጣ በ31ኛ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ31ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ በግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 4 ይከፈታል፡፡
8ኛ. የጨረታው መዝጊያ ወይም መከፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
9ኛ. ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉለውም።
10ኛ. የቀረበው ዋጋ VAT መጨመሩን እና አለመጨሩን መግልፅ አለባቸው።
11ኛ አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈራረሙ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ዋጋ Performance Security/ 10% ያስገባውን ማስያዝ አለባቸው፡፡
12ኛ. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- ስ.ቁ 0473312048 / 0473312145/0935176016
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ
ቦንጋ
