Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara National Regional State Education Bureau (የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ)
  • Address ባህር ዳር ከተማ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-2-26-62-67
  • Websitehttps://anrseb.gov.et/
  • Deadline03 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2026-01-03 00:00:00
  • Categories Car Decoration Materials , Tire And Spare Parts

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ 2018 ዓ.ም በመደበኛ በጀት አመታዊ የመኪና ጐማና የመኪና ዲኮር እንዲሁም በድጋሚ የወጣ የጅፒኤስ /GPS/ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 11/2017

 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ 2018 . በመደበኛ በጀት አመታዊ የመኪና ጐማና የመኪና ዲኮር እንዲሁም በድጋሚ የወጣ የጅፒኤስ /GPS/ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች፡-

  1. በሚወዳደሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ መሆን አለባቸዉ።
  4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሰውን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  6. የግዥ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል። ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 13/15 የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/BID BOND/ ለሚወዳደሩበት ግዥ ዓይነት መኪና ጐማ ከነካላማዳሪው 70,000.00 /ሰባ ሺህ ብር/ የመኪና ዲኮር /50,000.00/ሃምሳ ሺህ ብር/ ጅፒኤስ 50,000.00/ሃምሳ ሺህ ብር/ ግዥ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
  8. የጨረታ ሰነድ ተሞልቶ ከጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ጋር ተያይዞ በፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የሞሉትን የግዥ ዓይነት በመጥቀስ ግልጽ ጨረታ የሚል ተፅፎበት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት እና 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን መግባት ይኖርበታል።
  9. ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ትምህርት ቢሮ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ክፍል ጨረታው ይከፈታል።
  10. የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  11. ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ አብክመ ትምህርት ቢሮ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል በግንባር በመቅረብ በፋክስ ቁጥር 058 222 0814 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 6267/058 320 9939/በመደወል ማግኘት ይቻላል።
  12. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ

Save Tender