በአማራ ብሄራዊ ከልላዊ መንግስት በዋግ ኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓም በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደሩ ንግድ ጽ/ቤት የገበያ ማእከል የህንጻ ግንባታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
ሃገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ከልላዊ መንግስት በዋግ ኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓም በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደሩ ንግድ ጽ/ቤት የገበያ ማእከል የህንጻ ግንባታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛውም ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- ከሚወዳደሩበት ግንባታ ጋር የተዛመደ፣ በዘመኑ የታደሠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
- ማንኛውም ተጫራች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የሚወዳደሩበት ደረጃ BC ከደረጃ 4/አራት/ እና ከዚያ በላይ GC ከደረጃ 5 /አምስት/ እና ከዚያ በላይ ያላቸው ብቻ
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ስነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
- የግንባታውን ዓይነትና ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ያገኙታል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከግ/ፋ/አስ/ር ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 ማግኘት ይቻላል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር ወይንም የግንባታውን ጠቅላላ ዋጋ 500,000 /አምስት መቶ ሺ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒአ)ወይንም ጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከፋይናሻል የመጫረቻ ፖስታ ጋር ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 ቀን ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት የምትችሉ መሆኑን
- የቴክኒካል ወይም ሌሎች የብቃት ማረጋገጫ የመጫረቻ ሰነዱን ለብቻው በአንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
- የፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዱን ለብቻው በአንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ታሽጎ መቅረብ ያለበት ሲሆን የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከፋይናንሻል ሰነድ /ፖስታ/ ጋር በአንድ ላይ በማሸግ በሰ/ከ/አስ/ር/ግ/ፋ/ን/አስ/ር/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ31ኛው ቀን ከጠዋቱ ከ2፡30 እስከ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚሁ በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በሰ/ከ/አስ/ር/ግ/ፋ/ን/አስ/ር/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 ከጠዋቱ 4፡00 ሰእት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሠአት በግልፅ ይከፈታል፣
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
- ጨረታው ተከፍቶ አሸናፊ ከሆኑ የጨረታውን ውል ማስከበሪያ ያቀረቡትን የጠቅላላ ዋጋ ድምር 25% በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ በማስያዝ አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸበት ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ አሸናፊው የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መውሰድ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የካለንደር በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በመንግስት ስራ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ጊዜ ይከፈታል፡፡
- በተጫራቾች የሚቀርበው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራች ውድቅ ይሆናል፡፡
- በአጠቃላይ በዚህ ጨረታ የሚጫረት ማንኛውም ተጫራች ተሻሽሎ በወጣው በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ በቁጥር በአብክመ ገ/በ/ከቢ/01/02 በቀን 15/09/2014 ዓ/ም የወጣው ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር የተያያዘው የመመዘኛ መስፈርት ውስጥ የሚካተቱ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በአማራ ብሄራዊ መንግስት በወጣው የግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1/2003 አንቀጽ 20.1 ስር ባሉት ይገመገማል፡፡
- ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በሰ/ከ/አስ/ር/ግ/ፋ/ን/አስ/ር/ደ/የስ/ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0334401040/41 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሰቆጣ ከተማ አስ/ር ገንዘብ ጽ/ቤት
