የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የመፀዳጃ ቤትና ቧንቧ መለዋወጫ ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ፣ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መፈፀም ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EEP/NP/NCB/12/2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የመፀዳጃ ቤትና ቧንቧ መለዋወጫ ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ፣ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መፈፀም ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚሚሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድህረ-ገጽ (EGP) ላይ የተመዘገቡ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው።
- በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል።
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ህንፃ ቁጥር-11 1ኛ ፎቅ በሚገኘው ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺ) በመክፈል እና የጨረታ ሰነዱን ህንፃ ቁጥር-9 1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 201 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከዚህ በላይ የተመለከቱትን የመፀዳጃ ቤትና ቧንቧ መለዋወጫ ግዥ የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዳቸውን ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/NP/NCB/12/2018 የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ የሚል ምልክት በማድረግ ከታች በተቀመጠው ሰንጠረዥ መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
|
No. |
የግዥው አይነት/ Description |
የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
የመፀዳጃ ቤትና ቧንቧ መለዋወጫ ግዥ |
ብር 45,000.00 (አርባ አምስት ሺህ ብር) |
ታህሳስ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት |
ታህሳስ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት |
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-558-06-27 መደወል ይችላሉ።
- ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
