የሚአ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት የሚ/አ/ከ/አስ/ር ዋና ማዘጋጃ ቤት በባለቤትነት ለሚያሰራው ሎት 1 የሚ/አ/ከ/አስ/ር መግቢያ እና ሎት 2 የሚ/አ/ከ/አስ/ር መውጫ በግንባታ ስራ የተደራጁ ማህበራቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የሚአ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት የሚ/አ/ከ/አስ/ር ዋና ማዘጋጃ ቤት በባለቤትነት ለሚያሰራው
- ሎት 1 የሚ/አ/ከ/አስ/ር መግቢያ
- ሎት 2 የሚ/አ/ከ/አስ/ር መውጫ
በግንባታ ስራ የተደራጁ ማህበራቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላል፡፡
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- ግብር ስለመክፈላቸው ከገቢዎች መ/ቤት ክሊራንስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ከግዥ ኬዝ ቲም የሥራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ከፍለው በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ከአደራጅ መ/ቤት 5 የማህበር አባላት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ሞልተው ሲመልሱ ቴክኒካሉን 1 ኦርጅናልና 2 ኮፒ ፋይናንሻሉን 1 ኦርጅናልና 2 ኮፒ በሁለት ፖስታ በማድረግ እና በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ እና ለሎት ሁለት 25,000 /ሃያ አምስት ሺ ብር/ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ቼክ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፣ በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ክሬዲት ለሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በማለት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ 22ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ4፡00 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
- በጨረታው ማስታወቂያ ላይ የትርጉም ስህተት ቢኖር በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፀው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
- ሰነዱን ሞልተው ወደ ጨረታ ሳጥን ለማስገባት ሲመጡ ተመዝግበውና ፈርመው ማስገባት አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
