በአብክመ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የስሪንቃ ግብርና ምርምር ማዕከል በ2018 በጀት ዓመት አገልግሎታቸውን የጨረሱ የተከማቹ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች በሀራጅ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አሳውጆ ሸጦ ማስወገድ ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ ሀራጅ ሽያጭ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የስሪንቃ ግብርና ምርምር ማዕከል በ2018 በጀት ዓመት አገልግሎታቸውን የጨረሱ የተከማቹ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች በሀራጅ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አሳውጆ ሸጦ ማስወገድ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት በሎት የተለያዩ ቁርጥራጭ የተከማቹ የተለያዩ መጠን ያላቸው ብረታ ብረቶች
ስለሆነም ተጫራቾች ለመሳተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡-
- በስራ ዘርፍ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የቫት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ያላቸው፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በትክክል ሞልተው በኦርጅናልና በኮፒ ሰነድ በ 2 በተለያየ ፖስታ አሽገው ለዚህው የተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል
- ውድድሩ በድምር ዋጋ ወይም በሎት መሆኑ ታውቆ ሁሉም መሙላት አለባቸው፤
- ተጫራች አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት መጥተው ውል መውሰድ እና በውሉ ላይ በተቀመጠው ቀነ ገደብ በውሉ መሰረት መፈፀም አለበት ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በስሪንቃ ግብርና ምርምር ማዕከል ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ድረስ በመምጣት የማይመለስ 50.00 /አምሳ ብር ብቻ/ በመክፈል መወሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን ከጧቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚህው ቀን ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ማንኛውንም ማስረጃዎች ሆነ ጥሬ ገንዘብ በእጅ ይዞ መቅረብ አይችልም ፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፋበትን ዋጋ ገቢ ሳያደርጉ እቃውን መውሰድ አይችሉም
- የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን የተሳሳተ ጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል በሕግም ያስጠይቃል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በካላንደር ዝግ ከሆነ የሚቀጥለው ስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን የሚሞላው ከመነሻ ዋጋው በላይ መሆን አለበት፡፡ ንብረቱን በአካል ማየት አለባቸው፡፡
- በጨረታው አሸናፊ ከሆነ የውል ማስከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላ ዋጋ 10% (Cpo) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም ኢንሹራንስ ማስያዝ ይኖርበታል ውሉም ሲጠናቀቅ ተመላሽ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሞሉትን ዋጋ 1% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በመ/ቤታችን ገቢ ደረሰኝ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ያስያዙት Cpo በመሂ 1 የገቢ ደረሰኝ ከኦርጅናል ጨረታ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
ለበለጠ መረጃ 0333300090 /ሰሜን ወሎ ዞን ስሪንቃ/
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የስሪንቃ ግብርና ምርምር ማዕከል
