በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በከተማው ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የሚሠሩ ግንባታዎችን ለማሠራት እና የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
ሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ግ/ፋ/ን/–0031/2018 ዓ.ም
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በከተማው ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የሚሠሩ ግንባታዎችን ለማሠራት ማለትም 1ኛ ከሕዝብ ላይብረሪ ፊት ለፊት መሸጋገሪያ ድልድይ ግንባታ ሥራ ደረጃ 6 /ስድስት/ እና ከዚያ በላይ በRC & GC 2ኛ ከምስጌ ደምሴ እስከ ወንዙ ድረስ የውሃ ማፋሰሻ ካናል ሥራ ደረጃ 8/ስምንት እና ከዚያ በላይ RC & GC 3ኛ ከተማ ማዘጋጃ ግቢ ውስጥ የጋራ ሽንት ቤት ግንባታ ሥራ ደረጃ 8 /ስምንት/ እና ከዚያ በላይ BC& GC 4ኛ ከመርጌታ ልብስ ወርቅ ወደ ምስጌ ደምሴ ድጋፍ ግንብ ሥራ ደረጃ 8 /ስምንት/ እና ከዚያ በላይ BC& GC 5ኛ ሌተናል ጀነራል ሀይሉ ከበደ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት መድኃኔዓለም ት/ቤት እና አዝባ ት/ቤት ጥገና ሥራ ደረጃ 9 /ዘጠኝ/ እና ከዚያ በላይ BC& GC 6ኛ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 7ኛ የጽሕፈት መሣሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባትና መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ
|
የግንባታው አይነት እና የዕቃው አይነት
|
የጨረታ ማስከበሪያ ብር
|
|
1
|
ከሕዝብ ላይብረሪ ፊት ለፊት መሸጋገሪያ ድልድይ ግንባታ ሥራ
|
283015
|
|
2
|
ከምስጌ ደምሴ እስከ ወንዙ ድረስ የውሃ ማፋሰሻ ካናል ሥራ
|
91221
|
|
3
|
ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ የጋራ ሽንት ቤት ግንባታ ሥራ
|
75238
|
|
4
|
ከመርጌታ ልብሰ ወርቅ እስከ ምስጌ ደምሴ ድጋፍ ግንብ ሥራ
|
89719
|
|
5
|
ሌተናል ጀነራል ሀይሉ ከበደ የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤት መድኃኔዓለም ት/ቤት አዝባ ት/ቤት ጥገና ሥራ
|
57000
|
|
6
|
የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
|
950
|
|
7
|
የጽሕፈት መሣሪያዎች
|
3619
|
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በየዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
- የግዥ መጠኑ ብር 200.000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ማንኛውም ተጫራች የተጨማሪ እሴት ታስክ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
- የግንባታ ዝርዝር መግለጫ እና የሚገዙ እቃዎችን አይነት (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ያገኙታል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያአንዳንዱ ለግንባታ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ ሲሆን ለእቃ ሰነድ መግዣ 100 አነድ መቶ ብር/ በመክፈል ከዋና ገንዘብ ያዝ ቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ይቻላል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ግንባታ ወይም እቃ ከላይ በተገለጸው ገንዘብ መሰረት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ጨረታዉ ከተከፈተ ለተከታታይ 60 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀን ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
- ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግ/ፋ/ን/አስ/ር/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚሁ በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግ/ፋ/ን/አስ/ር/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4:30 በግልጽ ይከፈታል፣
- የሂሳብ ስሌት /አርትሜቲክ ቼh/ በግዥ ፈጻሚው መ/ቤቱ ባለሞያ ከሚስተካከለው ውጪ በተጫራቾች የሚቀርበው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በነጠላና በጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውጪ ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም የመንግሥት ሥራ ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ጊዜና ሰአት ይከፈታል፡፡
- ማንኛም ተጫራች ላሸነፈው ፕሮጀክት ሁሉንም ለሥራ የሚያስፈልጉ የማቴሪያል አይነቶች ቴስት በራሱ ወጪ ከሚመለከተው ቦታ ወስዶ አሠርቶ የማምጣት ግዴታ አለበት።
- የአካባቢ እና ማህበራዊ የተጽእኖ ማቃለያ ዕቅድ እና የአካባቢ ደህንነት የትግበራ መመሪያ ተግባራዊ የሚያደርግ መሆን አለበት።
- ማንኛውም ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር በአዲሱ በተሻሻለው መመሪያ መሰረት በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው ጠቅላላ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት (አርቲሜቲክ ቼክ/ ከተሠራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ 2.5 ድረሰ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ የበለጠ ልዩነት ካጋጠመ ከውድድር ውጪ ይሆናል።
- ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግ/ፋ/ን/አስ/ር/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በአካል በመገኘት ወይንም በስልክ ቁጥር 033 540 7058 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የሰቆጣ ከተማ አስ/ር/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት
