የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ለመብራት ዝርጋታ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ለመብራት ዝርጋታ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ተጫራቾች፡-
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል ክሊራንስ፣ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያላቸው እና በጨረታ ለመሳተፍ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው።
- የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ወይም ሂሳብ ክፍል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ቅዳሜና እሁድ የመስሪያ ቤቱ የስራ ቀናት አይደሉም።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ በጨረታ ሰነዱ ላይ ለተጠቀሱት ዕቃዎች ዋጋ ዝርዝር በመሙላት በአገልግሎቱ ዋና መ/ቤት የግዥ ቡድን ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እስከ ቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የተጫራቾች ዋጋ በግልጽ የሚነበብና ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን ይኖርበታል። ስርዝ ድልዝ ያለበት የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ በ4፡30 ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት /Refugees & Returnees Service/ በሚል የተዘጋጀ የባንክ ማዘዣ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ጥሪ በደረሰው በ05 /አምስት/ ቀናት ውስጥ በአገልግሎቱ ዋና መ/ቤት ቀርቦ የሥራ ውል መፈረም አለበት።
- አሸናፊው ጥሪ በደረሰው በአምስት ቀናት ውስጥ በአገልግሎቱ ዋና መ/ቤት ቀርቦ ውል ካልፈረመ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመ/ቤቱ ገቢ ይሆናል።
- የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የእንቁላል ፋብሪካ አደባባይን ሳይሻገሩ ከፌደራል ፖሊስ ክበብ ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር 09-97-23-66-31
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት
