በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የአንድ ፑል ማዕከል ተጠቃሚ በሆነው በጌዴኦ ዞን ግብርና መምሪያ የአጥር ግሪል እና የጥበቃ ቤት ግንባታ ከዘርፉ የተሰማሩትን ማህበራትን በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።
የግንባታ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የአንድ ፑል ማዕከል ተጠቃሚ በሆነው በጌዴኦ ዞን ግብርና መምሪያ የአጥር ግሪል እና የጥበቃ ቤት ግንባታ ከዘርፉ የተሰማሩትን ማህበራትን በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።
ለዚህ በመስኩ የተሠማራችሁ ተጫራቾች፡-
-
- በደረጃ 8 የተደራጁ ማህበራት
- የዘመኑን ግብር የከፈለና የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ ያለውና ማቅረብ የሚችል
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- በከተማና መሠረተ ልማት ሚንስቴር የተመዘገቡና የታደሰ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- በኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የተመዘገበና የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የ2017 በጀት ዓመት ከግብር ነጻ መሆናቸውን የሚገልጽ ከገቢዎች የተሰጠ ሰርተፍኬት የሚያቀርብ
- በክልሉ እና በዞናችን ውስጥ በግንባታ ሥራ ላይ ተሰማርተው የመልካም ሥራ አፈጻጸም ያላቸውና ስራዎችን ያላስተጓጎሉ ውል ያላቋረጡ መሆን ይገባቸዋል፤
- የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዘወትር በስራ ሰዓት በመቅረብ የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በመውሰድ ቴክኒካል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ሰነድ እንዲሁም ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ የጨረታ ሰነድ እያንዳንዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ አንድ ላይ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት በ22ኛው ቀን ይሆናል፡፡
- ኦርጅናል ሰነድ ላይ ማንኛውም አይነት ስርዝ ድልዝ በሚታይ መልኩ በድጋሚ መጻፍ አለበት፡፡
- በእያንዳዱ የጨረታ ሰነድ ላይ የማህበሩ ማህተምና ፊርማ ማረፍ አለበት፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ለ21 ተከታታይ ቀን ከዋለ በኋላ በ22ኛ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በዚያው ዕለት 4:30 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾ የጨረታ ማስከበሪያ 40,000 (አርባ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እና ከታወቀ በባንክ የሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም ለ90 (60+30) ቀን የሚቆይ በባንክ ዋስትና ሆኖ በጥሬ ገንዘብ እና በኢንሹራንስ ዋስትና መቅረብ አይቻልም፡፡
- ጨረታው የሚገመገመው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት እንደገና ተሻሽሎ በወጣ የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 70/2017 እና በዚህ መመሪያ ላይ ማብራሪያና ማሻሻያ በተደረገው መሠረት ነው።
በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በመሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0461310108 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
