ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ/የተ.የግ.ማህበር የ ኤሌክትሪክ ዕቃዎች ግዥን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ
ቁጥር EAC 017/2018
- ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ/የተ.የግ.ማህበር የ ኤሌክትሪክ ዕቃዎች ግዥን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከታህሳስ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ከታህሳስ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30- 6፡30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7:30 -11:00 ድረስ "ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማ ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴያሪ ጀርባ ከኤልፎር አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮ አግሪ ሴፍት - ሕንጻ ላይ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት
- አንድ ዋና /Original/ የጨረታ ሰነድ ለብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጐ
- አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ ታሽጐ እንዲሁም፣
- ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ የታሸገ መሆን አለበት፡፡
- በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፤ የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ግዥን የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ከመቶ/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም ኮንዲሽናል ባንክ ጋራንቲ ለኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ከታህሳስ 27 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 208 ሲሆን፣ ጨረታውን የመከፈቻ ቀን ከታህሳስ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 106 ይሆናል።
- ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ከጨረታው የሚሠረዝ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0116676204 ፋክስ ቁጥር 0116732006 መጠቀም ይችላሉ፡፡
- ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ/የተ የግ ማህበር
