የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ለሸንኮራ እርሻ የሚያገለግለውን ማሳ ምንጣሮ ለማሰራት ከዚህ በታች የተገለፀውን የዶዘር ኪራይ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ለሸንኮራ እርሻ የሚያገለግለውን ማሳ ምንጣሮ ለማሰራት ከዚህ በታች የተገለፀውን የዶዘር ኪራይ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ጥቅል አንድ፡- ዶዘር ኪራይ (D7 Bulldozer/ Dozer) በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
- ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን የሀገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች ለአንዱ ጥቅል የማይመስስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሠዓት ሜከሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ህንፃ ግዥ ቡድን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 215 የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ገዝተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሲገዙ የንግድ ፈቃድ ይዘው መቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሠነድ ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ የአቅራቢዎች የምዝገባ ሠርተፍኬት እና ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) በሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ (Proforma invoice) ላይ በማዘጋጀት በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እ.ኢ.አ. ጥር 05 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ሜክሲኮ ፊሊፕስ ሕንጻ ቢሮ ቁጥር 119 ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በእለቱ ጥር 05 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 119 ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ፋብሪካው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 0115-505607, 0115-505633
ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ሕንፃ
አዲስ አበባ
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ
