Tender Detail

Tender Details

  • Company South Ethiopia Regional State Roads Authority (የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን)
  • Address ዲላ ከተማ : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0916866262
  • Website
  • Deadline17 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price400.00
  • opening date2026-01-17 00:00:00
  • Categories Car Decoration Materials , Tire And Spare Parts

የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ከላይ እንደተጠቀሰው ለቀላል ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል በቁጥር 160 ጎማዎች እስከነ ውስጥ ላስቲካቸው እና ፍላፕ (7.50R16 Tyre with Inner tube & Flaps) ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

የቀላል ተሽከርካሪ ጎማ (7.50R16) ግዥ ለመፈፀም

የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ደመባ ቁጥር 08/2018

 

የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ከላይ እንደተጠቀሰው ለቀላል ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል በቁጥር 160 ጎማዎች እስከነ ውስጥ ላስቲካቸው እና ፍላፕ (7.50R16 Tyre with Inner tube & Flaps) ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ላላቸው ግዥዎች የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ፣በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆናቸው የምዝገባ ማስረጃ እና በጨረታ ለመሳተፍ ከሚመለከተው የመንግስት አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳብ የሚያቀርቡበትን የጨረታ ሰነድ የቴክኒክ እና ፋይናንሻሉን አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ የጨረታ ማስከበሪያው ደግሞ በተለየ ፖስታ በማድረግ ስማቸውን ፊርማቸውን አድራሻቸውንና የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት በትክክል ማስፈር አለባቸው።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከባለስልጣኑ ዋና ቢሮ ቁጥር 05 መውሰድ ይችላሉ።
  4. አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 800 ድረስ ይሆናል። ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 830 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
  5. ተጫራቾች በእንግሊዘኛ የተጻፈውን የቴክኒክ ዝርዝር መግለጫ በሚጠይቀው መሠረት መሙላት ይጠበቅባቸዋል። ይህንን ያልሞሉት የቴክኒክ ዝርዝር መግለጫ እንዳልቀረበ ተቆጥሮ የማቅረብያ ሰነዱ ውድቅ ይደረጋል።
  6. ተጫራቾች ብር 88,000.00/ሰማንያ ስምንት ሺህ ብር/ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ/ሲፒኦ/ ወይም በባንከ ዋስትና ወይም ከኢንሹራስ ዋስትና በቀር በግዥ መመሪያው ላይ ባሉ አማራጮች በፈለጉት ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም።
  8. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ይሰረዛሉ። ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ይወረሳሉ። ለወደፊቱም /ቤቱ በሚያወጣው የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ ይደረጋል።
  9. ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ 45 ቀናት ፀንቶ መቆየት አለበት።
  10. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት መሆኑ ከተገለፀለት አምስት /5/ ቀናት ውስጥ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና / Performance Bond 10% በባንክ ጋራንቲ ወይም በሲፒኦ በማቅረብ ውል መፈረም ይኖርበታል። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ውል ለመፈረም ፈቃደኛ ያልሆነ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ይወረሳል።

ለበለጠ መረጃ፡- ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።

የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን

ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም

የፖ..

የስልክ ቁጥር 09 23 69 00 58 / 09 32 70 88 47

ዲላ ኢትዮጵያ

 

የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን

Save Tender