Tender Detail

Tender Details


በጉምሩክ ኮሚሽን በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜያት የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ባለመፈጸሙ ምክንያት እና በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ልዩ ልዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የአ/ ኤርፖርት ጉምሩክ //ቤት ልዩ ልዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ ጨረታ ቁጥር 49/2018 50/2018 51/2018 52/2018 53/2018 54/2018 እና 55/2018

በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ //ቤት በተለያዩ ጊዜያት የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ባለመፈጸሙ ምክንያት እና በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሞባይሎች የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ጌጣጌጥ እና አካላት፣ አልባሳት፣ ጫማዎች፣ የብርጌጣጌጥ ፕላትኒየሚ ጊርቦክስ፣ የመኪና ሞተር እና ሌሎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ ጨረታ ቁጥር 49/2018 በቀን 04/5/2018 .ም፣ ጨረታ ቁጥር 50/2018 በቀን 07/5/2018 . ጨረታ ቁጥር 51/2018 በቀን 14/5/2018 .ም፤ ጨረታ ቁጥር 52/2018 በቀን 18/5/2018 . ጨረታ ቁጥር 53/2018 በቀን 21/5/2018 .ም፤ ጨረታ ቁጥር 54/2018 በቀን 25/5/2018 . እና ጨረታ ቁጥር 55/2018 በቀን 28/5/2018 . በመሆኑ የቀጣይ 2018 በጀት ዓመት ዕቅድ በተፈለገው መጠን ለማሳካት ለሁሉም ተደራሽነት ባለው መልኩ በጋዜጣ ማስታወቂያ እንዲወጣልን እየጠየቅ' ዝርዝር መረጃ ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 1-14 እንገልፃለን፡፡

በመሆኑም:-

  1. በቅ//ቤቱ ለሚካሄደው ጨረታ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት እና የዘመኑ ግብር የተከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ማንኛውም የግልጽ ጨረታ ተጫራች ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ 200-600 ከሰዓት በኋላ 700-1100 እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት 200-600 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ //ቤት ገርጂ ጉምሩክ መጋዘን ቅጥር ግቢ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላል፡፡
  3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) CUSTOMS COMMISSON ADDIS ABABA AIRPORI CUSTOM BRANCH OFFICE ስም ማሠራት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ካርጎ መጋዘን እና ገርጂ መጋዘን እስከ ጥር 04/2017 .ም፣ ጥር 07/2018 ጥር 14/2018 ጥር 18/2018 ጥር 21/2018 .ም፣ ጥር 25/2018 እና ጥር 28/2018 . ከቀኑ 800 ዘግቶ በዛው ቀን 815 የሚከፈት ይሆናል፡፡
  5. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ለጨረታው የሚሰጡትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዘው በቀረቡት ቅጾች መሠረት ለመረጡት የዕቃዎች ኮድ የተሰጠ ዋጋ፣ የተጫራቾች ስም፣ አድራሻ ፈርማና የጨረታ ማስከበሪያ ..(CPO) እና ከላይ በተ. 1 የተገለጹትን ሰነዶች ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ በመፈረም አዲስ አበባ ኤርፖርት //ቤት ገርጂ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነዱ የሰጠውን መግዣ ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የሰጠውን የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ የጨረታው ውጤት እስከሚታወቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊዎች ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ 05 (አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለባቸው።
  9. ከላይ በተ/ 8 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ንብረቱን ተረከቦ ያልወሰደ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት .. (CPO) ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
  10. በተራ ቁጥር 01-09 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም በሐራጅ ጨረታ ቁጥር 40/2018 በቀን 02/4/2018 . ጨረታ ቁጥር 49/2018 በቀን 04/5/2018 .ም፣ ጨረታ ቁጥር 50/2018 በቀን 07/5/2018 .ም፣ ጨረታ ቁጥር 51/2018 በቀን 14/5/2018 .ም፣ ጨረታ ቁጥር 52/2018 በቀን 18/5/2018 .ም፣ ጨረታ ቁጥር 53/2018 በቀን 21/5/2018 .ም፣ ጨረታ ቁጥር 54/2018 በቀን 25/5/2018 . እና ጨረታ ቁጥር 55/2018 በቀን 28/5/2018 . ከጠዋቱ 400 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የምናካሂድ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ እያሳወቅን፣ የዕቃዎችን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ //ቤት ገርጂ እና ካርጎ ውርስ መጋዘን በመገኘት መመልከት ይቻላል፡፡
  11. በሐራጅ ጨረታ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ/ APHC CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA AIRPORT CUSTOM BRANCH OFFICE ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  12. ለጨረታ የቀረቡት የዕቃዎች ዋጋ ከቫት በፊት የተሰጠ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  13. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች በተናጠል ሳይሆን ለጨረታው ሰነዱ በተሰጠ ኮድ ቁጥር ብቻ የሚሸጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  14. //ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ መረጃ ቦሌ ኤርፖርት በስልክ ቁጥር 0116684537 እና 0116684193 ደውለው ይጠይቁ።

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የአ/ ኤርፖርት ጉምሩክ //ቤት

 

Save Tender