Tender Detail

Tender Details

  • Company የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
  • Address ሀዋሳ ከተማ አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-212-13-34
  • Website
  • Deadline16 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2026-01-16 00:00:00
  • Categories Sport Materials And Sportswear

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ባህል፤ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ካቀዳቸው ግዥዎች መካከል አንዱ ለሀላፊዎችና ስፖርት ባለሙያዎች የስፖርት ትጥቅ ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በማወዳደር በዘርፉ ፈቃድ ካለው አቅራቢ ተጫራቾች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሀዋሳ ከተማ አስ////መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ባህል፤ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ 2018 በጀት ዓመት ካቀዳቸው ግዥዎች መካከል አንዱ ለሀላፊዎችና ስፖርት ባለሙያዎች የስፖርት ትጥቅ ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በማወዳደር በዘርፉ ፈቃድ ካለው አቅራቢ ተጫራቾች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

1.     በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢ/ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡-

2.     በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ

3.     የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

4.     ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣

5.     የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣

6.     የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፤

7.     የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ) አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 /ለአሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ወስዶ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ፡፡

8.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡

9.     ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ (ፋይናንሻል እና ቴክኒካል) በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አሥር) ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

10. ጨረታው 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 330 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከጠዋቱ 400 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ፤ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡

11. ተጫራቾች ጨረታ ሲያስገቡ ናሙና ይዞ መቅረብ አለበት፡፡

12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

ስልክ ቁጥር 046-212-13-34

 

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ//መምሪያ

Save Tender