Tender Detail

Tender Details

  • Company የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
  • Address ሀዋሳ ከተማ አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-212-13-34
  • Website
  • Deadline16 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2026-01-16 00:00:00
  • Categories Plastic Raw Materials And Products , Vehicles Rent , Materials , Cargo Vehicle , Construction Vehicle

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/መምሪያ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ሥር የሚገኙ የገጠር ቀበሌ ተደራሽ ሥራዎችን ቀበሌን ከቀበሌ የሚያገናኙ የመንገድ ሥራ በሀዌላ ቱላ ቀበሌያት ለማሰራት በ2018 በጀት ዓመት በታቀደው መሰረት ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በማወዳደር በየዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሀዋሳ ከተማ አስ//መምሪያ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ሥር የሚገኙ የገጠር ቀበሌ ተደራሽ ሥራዎችን ቀበሌን ከቀበሌ የሚያገናኙ የመንገድ ሥራ በሀዌላ ቱላ ቀበሌያት ለማሰራት 2018 በጀት ዓመት በታቀደው መሰረት ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በማወዳደር በየዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት፡-

·        ቱላ ውሃ ታንከር በሀዌላ ሊዳ ድንበር ለማሰራት ሎት 01/2018

·        ሰሌክት ማቴሪያል ገዝቶ እስከ ቦታው አምጥቶ ማስረከብ፡- ሎት 02/2018

·        የማሽነሪና የተሽከሪካሪዎች ኪራይ፡- ሎት 03/2018

·        ግሬደር የፈረስ ጉልበት 214 HP ብዛት 1

·        ሮለር ኮምክተር የፈረስ ጉልበት 120 HP ብዛት 1

·        ገልባጭ መኪና/ሲኖትራክ የፈረስ ጉልበት 336 HP ብዛት 3

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር ይችላሉ፡-

1.     በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣

2.     የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3.     ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣

4.     የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣

5.     ከሚመለከተው /ቤት የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፤

6.     የተመሰረቱበት ዓመት // ማሽነሪዎች 2014 እና መኪና 2015

7.     የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ) አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 /ለአሥር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

8.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡

9.     ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ በማሽን ተወዳዳሪዎች ቴክኒክ ሰነድ ጭምር በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አሥር) ተከታታይ ቀናት ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዥ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

10. ጨረታው 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 330 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከጠዋት 400 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ፤ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል፡፡

11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ስልክ ቁጥር 046-212-13-34

 

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ//መምሪያ

Save Tender