በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍ/ቤት በ2018 ዓ.ም ከካፒታል በጀት እና ከመደበኛ በጀት ሞተር ብስክሌት፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን (ላፕ ቶፕ ኮምፒውተር፣ ዲስከ ቶፕ ፕሪንተር፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን/ እና የጽ/መሣሪያ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍ/ቤት በ2018 ዓ.ም ከካፒታል በጀት እና ከመደበኛ በጀት ሞተር ብስክሌት፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን (ላፕ ቶፕ ኮምፒውተር፣ ዲስከ ቶፕ ፕሪንተር፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን/ እና የጽ/መሣሪያ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች፡-
1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
2. ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ የሆነበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. ዝርዝር የጨረታ ሠነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በደቡብ ኢትዮጵያ ከልል መንግስት የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍ/ቤት የግዥ ክፍያ ንብረት አስ/ር ድጋፍ የሥራ ሂደት እየመጡ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመከፈል የጨረታ ሠነድ መግዛት ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒአ /CPO/ ከጨረታው ሠነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን የዋጋ ማቅረቢያ ሠነዶቻቸውን ኦርጅናሉን በፖስታ በማሸግ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ መጨረሻው ቀን ከቀኑ 10፡00 ድረስ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ የጨረታ ሠነዶቻቸውን ማስገባት አለባቸው፤ ጥራቱን በጥንቃቄ እናያለን።
6. ዝርዝር የጨረታ ሠነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አሥራ አምስት ቀናት/ ከቀኑ 10፡00 ድረስ በሣጥኑ መጨመር አለባቸው፡፡ በዕለቱ 11፡00 ታሽጎ በሚቀጥለው ቀን ማለትም በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡30 ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በሠነዱ ከተባለው ውጪ ማቅረብ አይቻልም።
7. በጨረታው ሠነድ ላይ የተፃፈውን የዕቃ ዓይነት ተጫራቾች በትክክል መሙላት አለባቸው። የሚያቀርቧቸው ዋጋ ከቫት ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
8. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ዕቃውን እስከ መ/ቤቱ ድረስ ያቀርባል።
ፍርድ ቤቱ ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን መለወጥ ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በደቡብ ኢትዮጰያ ክልላዊ መንግስት የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍ/ቤት
