የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2018 የበጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2018 የበጀት ዓመት፡-
1. ፎቶ ኮፒ፤ ፕሪንተር እና ፕሮጀክተር ለሁለተኛ ጊዜ ለማስጠገን
2. የፈሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ /ሥራ ለአንደኛ ጊዜ ለማሰራት
3. የተለያዩ የመኪና ጎማዎች ለሁለተኛ ጊዜ ለመግዛት እና
4. የ "Cardiotorasic" እቃዎች ለሁለተኛ ጊዜ ለመግዛት በግልፅ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላለችሁ፡፡
· የ2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ በዘርፉ ያልችሁ።
· ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆን መረጃ ማቅረብ የሚችል፡
· በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባችሁን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
· ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ ግዥ መ/ቤት ድረስ በራሱ ወጪ ማቅረብ የሚችል፡፡
· ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ኮፒና ኦሪጅናል ለየ ብቻ በተለያየ ፖስታ ማሸግ አለባቸው።
· ስርዝ ድልዝ ያለው፤ የማይታይ የጨረታ ሰንድ ወይም የዋጋ ዝርዝር ተቀባይት የለውም።
· ጨረታውን ከሸነፉ በኋላ የውል ማስከበሪያ የአሸነፉበትን ዋጋ 10% ማሰያዝ የሚችል፡፡
· ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኮሌጁ ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ክፍል ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ጨረታ ለየ ብቻ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ አለባቸው።
· የፈሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ሥራ ጨረታው የሚከፈተው በ15/05/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
· የፎቶ ኮፒ፣ ፕሪንተር እና ፕሮጀክተር ለማስጠገን ጨረታው የሚከፈተው 15/05/2018 ከቀኑ 9:30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
· የተለያዩ የመኪና ጎማዎች ጨረታው የሚከፈተው በ19/05/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
· P'Cardiotorasic" እቃዎች ጨረታው የሚከፈተው በ19/05/2018 ከቀኑ 9፡30 ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
· ተጫራቾች የሚሞሉትን ዋጋ በመስሪያ ቤቱ ሰነድ ብቻ ላይ መሆን አለበት፡፡
ጨረታው ማስከበሪያ፡-
1 ላይ ላለው ተራ ቁጥር ጨረታ 10,000 (አስር ሺህ) ብር
2-3 ላይ ላለው ተራ ቁጥር ጨረታ ለየ ብቻ 20,000 (ሃያ ሺህ) ብር እና
4 ላይ ላለው ተራ ቁጥር ጨረታ 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ብር በ"CBE, CBO, እና በSinge" ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
አዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0228123956 ደውለው መረዳት ይችላሉ፡፡
አዳማ ሆስፒታል ሚዲካል ኮሌጅ
