Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የዝቋላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዝቋላ ወረዳ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0334620050/53/49
  • Website
  • Deadline30 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00
  • opening date2026-01-30 00:00:00
  • Categories Building Materials

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በዝቋላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አማካኝነት 2018 በጀት አመት በመደበኛ በጀት በወረዳው ለሚገነባው G+3 አስተዳደር ህንፃ ለበርና እና ለመስኮት መስሪያ አገልግሎት የሚውል የጣውላ ፤ የአልሙኒየም እና ለወረዳው ሴከተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል የእስተሸነሪ ጨረታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት የሚከተሉ


የአገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ መስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በዝቋላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አማካኝነት 2018 በጀት አመት በመደበኛ በጀት በወረዳው ለሚገነባው G+3 አስተዳደር ህንፃ ለበርና እና ለመስኮት መስሪያ አገልግሎት የሚውል የጣውላ ፤ የአልሙኒየም እና ለወረዳው ሴከተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል የእስተሸነሪ ጨረታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤

2. የገብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ያላቸው፤

3. ከ200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት፡፡

4. ለመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን መረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡

5. የተጫራቾች ጨረታው ላይ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1 እስከ 4 የተጠቀሱትን እና ሌላም መረጃ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በሁለት ኦርጅናል እና ኮፒ ብለው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. የሁሉንም ዕቃዎች ዝርዝር /እስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

7. መ/ቤቱ ካስቀመጠው ውጪ በራሱ ጊዜ ስፔስፊኬሽን የጨመረና የቀነሰ ወይም ያስቀመጠ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡

8 ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 400/አራት መቶ ብር ብቻ በመከፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በዝ/ ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በመምጣት ጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እና በ16ኛው ቀን 2፡30-6፡00 በተዘጋጀው ሳጥን በማስገባት በዚያው ቀን 8፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በዝ/ ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በግልፅ ይከፈታል፡፡

 

9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበትን የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንከ በተረጋገጠ የከፍያ ትእዛዝ/በሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡

10 ተጫራቶች ከሚወዳደሩበት ሰነዱ ላይ ከአንዱ ዋጋው እና ጠቅላላ ዋጋው ላይ ስርዝ ድልዝ ያደረገ ጨረታው ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ፡፡

11. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ላይ ዋጋ ሲሞሉ የአንድ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ የሚለውን በጥንቃቄ ለያይተው መሙላት አለባቸው፡፡

12. ጨረታው ተከፍቶ አሸናፊ ከሆኑ የጨረታውን ውል ማስከበሪያ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ ድምር 10% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የባንከ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ በማስያዝ አሸናፊ መሆናቸውን ከተገለፅበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል መውሰድ አለበት፡፡

13. መ/ቤቱ በጨረታው ዙሪያ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

14. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም የመንግስት ስራ ዝግ ከሆነ የሚቀጥለው የስራ ቀንና ሰዓት ተመሳሳይ ጊዜ ይከፈታል፡፡

15. ማንኛውም ተጫራች ከአርጅናል ሰነዱ ላይ የንግድ ፍቃዱን ኮፒ አድርጎ ፖስታው ላይ የማያስገባ ወይም ኮፒ አድርጎ ፖስታው ላይ ሳያስገባ ውጭ ላይ የተወ ከውድድር ውጭ የሚሆን መሆኑን ይታወቅ፡፡

16. የጨረታው አሸናፊው አካል ውል ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ቀጥታ በአስቸኳይ በውሉ መሰረት ንብረቱን በሚገኘው ዝ/ወ/መ/ቤቶች ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡

17. ይህ ውድድር ለአንድ ዓመት ሙሉ ስለሆነ ከላይ የተዘረዘሩት እቃዎች በአመቱ ውስጥ ሲያስፈልግ የሚያቀርብ መሆኑን ይታወቅ ::

18. መረጃ 0334620050/53/49 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የዝቋላ ወራዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender