የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት በዋናው መስሪያ ቤት የሚገኘውን ነባሩ ህንፃ የቢሮ ውስጥ የእድሳት ስራዎችና ተዛማጅ የሆኑ የተለያዩ ስራዎችን ለማሰራት የኢንትሪዬር ዲዛይን፣ የኔትወርክ ዲዛይንና ገመድ ዝርጋታ፣ የግንባታ ማጠናቀቀ ስራ እና የቢሮ ሙሉ ዕቃ የዲዛይንና የገጠማ ስራዎች /Interior Design, Finishing Construction Work, Network Design and
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ኢሎአ/006/2018
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት በዋናው መስሪያ ቤት የሚገኘውን ነባሩ ህንፃ የቢሮ ውስጥ የእድሳት ስራዎችና ተዛማጅ የሆኑ የተለያዩ ስራዎችን ለማሰራት የኢንትሪዬር ዲዛይን፣ የኔትወርክ ዲዛይንና ገመድ ዝርጋታ፣ የግንባታ ማጠናቀቀ ስራ እና የቢሮ ሙሉ ዕቃ የዲዛይንና የገጠማ ስራዎች /Interior Design, Finishing Construction Work, Network Design and Cable Installation Work and Furnish Office Materials/ ላይ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ስራዎችን ማሰራት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ሁሉ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ስራ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ስም በተከፈተ የባንክ ሒሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ ዋናውን ማስረጃ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፣ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ያለባቸው ብር 250,000.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በሲ.ፒ.ኦ /C.PO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ /Irrevocable or unconditional Bank Guarantee from Recognized Bank of Ethiopia/ ማስያዝ አለባቸው።
ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተገለፁትን የቴክኒካል ሰነዶችን የያዘ አንድ ዋናና አንድ ቅጂ ለየብቻው እንዲሁም የፋይናንሻል ሰነድ የያዘ አንድ ዋናና አንድ ቅጂ ለየብቻው እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናውን ለየብቻው በፖስታ በማሸግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ እስከ ጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 በዓት ድረስ ብቻ ለዚሁ ስራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ አለባቸው።
ጨረታው ጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና መ/ቤት ይከፈታል። አገልግሎቱ ስለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-011-126-78-16 ደውሎ መረዳት ይቻላል።
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት
