በልደታ ክ/ከተማ ተስፋ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2018ዓ.ም በጀት ዓመት ጥቅል ግዢ ከዚህ በታች የተጠቀሰትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ህጋዊ አቅራቢዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መሳተፍ ይችላሉ፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በልደታ ክ/ከተማ ተስፋ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2018ዓ.ም በጀት ዓመት ጥቅል ግዢ ከዚህ በታች የተጠቀሰትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ህጋዊ አቅራቢዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ሎት ቋሚያ ቢሮእታ፣ ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 3. የደንብ ልብስ እና የብሄር ብሄርሰቦች ባህላዊ አልባሳት፡ ሎት 4, የስፖርት ትጥቅ፣ ሎት 5, ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 6, የህንጻ መሳርያ እቃዎች፣ ሎት7. አጋዥ መጽሀፎች፣ ሎት 8, የህክምና እቃዎች፣ ሎት 9. ህትመት፣ ሎት 10 ህንጻ እድሳት
1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የእቃ እቅራቢ ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ከመንግስት ግዢ ኤጀንሲ የተሰጠ የምስክር ወረቀት እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
2 ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ካደራጃቸው ባለስልጣን ደብዳቤ ለሚያመጡት የጨረታ ሰነድ በነፃ መውሰድና ሶስት ፐርሰንት ቅናሽ የሚደረግላቸው እራሳቸው ላመረቱት እቃና ቫልዩ አድ ላደረጉት እቃ መሆኑን እናሳውቃለን።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200(ሁለት መቶብር) በመከፈል ጨረታ በአዲስ ዘመንጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 10 የስራቀናት ውስጥ በት/ቤቱፋይናንስ ቢሮ በአካል ቀርቦ መግዛትይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዕቃ ዝርዝር ዋጋ እና በተራቁጥር 1 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች በታሸገ ኢንቨሎፕ በተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት ፋይናስ ቢሮ ማስረጃውን ከቫት ጋር እና ቫትን ሳያካትት ግልዕ በሆነ መንገድ ዋጋው ተለይቶ ማቅረብ አለባቸው::
5. የመወዳደሪያ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ለዋጋ መስጫ በተዘጋጀ ቦታ ያለቫት እና ከቫት ተለይተው መሰጠት ይኖርባቸዋል።
6 ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ 2 ቀናት በፊት ኦርጂናልና ደረጃውን የጠበቁ ናሙና በት/ቤቱ ንብረት ክፍል ገቢማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
7 የጨረታ ሳጥን ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት 10 ተከታታይ የስራቀናት በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰአት ታሽጎ በእለቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው በመንግስት የስራ ቀን ሆኖ ሰዓቱ እንደተጠበቀ ይሆናል፡፡ በአለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታ ሳጥን መክፈቻ ስነ-ስርዓቱን እያጓትትም፡፡
8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸንፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዢ ፈፃሚ መስርያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
9. የዘገየ ጨረታ በጨረታ መክፈቻ ቀን ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም::
10. ለጨረታ ከቀረቡት እታዎች ዝርዝር ውስጥ ት/ቤቱ እስከ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ
11. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎቶች የተጠቀሰውን ብር cpo በማሰራት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
|
ሎት |
ሎት 1 |
ሎት 2 |
ሎት3 |
ሎት 4 |
ሎት5 |
ሎት 6 |
ሎት 7 |
ሎት 8 |
ሎት 9 |
ሎት 10 |
|
ብር |
2000.00 |
2000.00 |
4000.00 |
4000.00 |
2000.00 |
3000.00 |
2000.00 |
2000.00 |
2000.00 |
2000.00 |
አድራሻ ፡-ከሳርቤት ወደ ወረዳ 04 በሚወስደው መንገድ በሚገኘው ተስፋ የመጀ ደ/ት ቤት ፋይናንስ ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
400m 00113 83-44-45-0113-83-47-3210920034824
በልደታ ክ/ከተማ ተስፋ የመጀ/ደ/ት/ቤት
