የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽህፈት ቤት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር- አ/አ/ብ/ፓ/ቅ/ጽ-01/2018
የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽህፈት ቤት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት፡- 1 የጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎች
ሎት፡- 2 የጽዳት ዕቃዎች
ሎት፡- 3 የመኪና ዲኮር
ሎት፡- 4 የአይሲቲ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
1.1 የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
1.2 የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው
1.3 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
1.4 የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እና ሰርተፊኬት ያላቸው
1.5 በግዥ ኤጀንሲ አቅራቢዎች ሊስት የተመዘገቡ እና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
1.6 ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ስለ ግብር አከፋፈል የሚገልጽ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
2 ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 400.00 (አራት መቶ) ብር በመክፈል ትራፊክ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የድርጅቱ ጽ/ቤት ስድስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁ 6-03 በግንባር በመቅረብ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ መግዛት ይችላሉ።
3 ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር)፣ ለአይሲቲ ዕቃዎች 35,000 (ሰላሳ አምስት ሺህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ብቻ በድርጅቱ ስም ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። ጨረታውን ያላሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ተመላሽ ይደረግላቸዋል። አሸናፊ ድርጅቶች አሸናፊነታቸው እንደተረጋገጠ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው።
4 ተፈላጊውን የጥራት ደረጃ ያልጠበቀ ዕቃ ማቅረብ ከአቅራቢነት ያሰርዛል።
5 ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ከውድድር ውጪ ይሆናል።
6 ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሎት በመለየት ዋጋቸውን ጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘጋጀው የዋጋ መሙያ ላይ ብቻ ከቫት በፊት ያለውን ዋጋ በመሙላት እና ኦሪጅናል እና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ እንዲሁም ቴክኒካል ሰነድ ከሲፒኦ ጋር ኦሪጅናል እና ኮፒውን ለብቻ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል። ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ በ1 ፖስታ ማሸግ ከጨረታ ውጪ ያደርጋል።
7 ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች በሙሉ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የአይሲቲ እቃዎች ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነዶቻቸውን በተለያየ ፖስታ በመለየት ማቅረብ አለባቸው።
8 ከጨረታ ሰነዱ ውጪ ተሞልቶ የሚቀርብ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም
9 ጨረታው ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በአየር ላይ ከዋለ በኋላ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ 7ኛ ፎቅ በግልጽ ይከፈታል። የጨረታ መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
10 የጨረታ ሂደቱን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከውድድር ውጪ ይሆናሉ።
11 አንዱ ድርጅት በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
12 መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-6-67-44-30 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት
