Tender Detail

Tender Details


የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለጎንደር ከተማ አስ/ትምህርት መምሪያና ለጎንደር ከተማ አስ/አሳ ሀብት ልማት መምሪያ ከዚህ በታች በዝርዝር ያስቀመጣቸውን የግንባታ ስራዎችን ለማሰራት እና የተለያዩ የግንባታ ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለጎንደር ከተማ አስ/ትምህርት መምሪያና ለጎንደር ከተማ አስ/አሳ ሀብት ልማት መምሪያ

·        በሎት 1 የህ ጠዳ የተጀመረውን ትምህርት ቤት 1 ብሎክ ባል 4 መማሪያ ክፍል ለመገንባት

·        በሎ 2 የላይ ጠዳ ትምህርት ቤት ተጨማሪ የመማሪያ ክፍል ግንባታ ስራ ለማሰራት

·        በሎት 3 የጎ//እስ የአላሃብት ልማት መምሪያ የእንስሳት ክሊኒክ የግንባታ ስራ ለማሰራት

·        በሎት 4 ለጎ//አስ/ትምህርት መምሪያ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የግንባታ ቁሳቁስ ግዥ ለመግዛት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ስለዚህ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን፡-

ማቅረብ የምትችሉት መረጃ፡-

1.     የዘመኑ የታደለ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ

2.     የግብር መለያ ቁጥር TIN/ ያላቸው

3.     የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርበታል

4.     የህንጻ ግንባታውን ለማሰራት ደረጃ 7 እና ከዘያ በላይ የሆኑ

5.     ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6.     የሚገነባውን የግንባታ የስራ ዝርዝርና የቁሳቁስ ግዥ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።

7.     ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 1% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

8.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል ጎን//አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 15 መውሰድ ይችላሉ።

9.     ተጫራቾች የመጫረቻ ሃሳባቸውን አንድ ወጥ በሆነ ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ጎን//አስ/ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።

10. ተጫራቾች ዋጋውን በሚሞሉበት ወቅት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።

11. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ሙሉ ስምና ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።

12. ለግንባታ ስራዎች የፋይናንስ ግምገማ የተወዳደሩ ተጫራቾች ቁጥር ቢያንስ 3 እና በላይ ከሆኑ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት /አርቲሜቲከ ቼክ/ ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ 2.5% ድረስ ከሆነ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ የበለጠ ልዩነት ካጋጠመ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡ እንዲሁም 3 በታች ከሆነ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት /አርቲሜቲክ / ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ 1% ድረስ ብቻ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ በላይ ከሆነ ከውድድር ውጭ ይሆናል።

13. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለተከታታይ 21 ቀናት በጎንደር /አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 11 በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው 22ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ታሽጎ 430 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ ጥሪአችንን አከብረው ባይገኙም ጨረታው በሌሉበት ይከፈታል፡፡ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰአት የሚከፈት ይሆናል።

14. ማንኛውም ተጫራች የሚቀርብ ቅሬታ ካለ ጨረታው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀን ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን 5 የስራ ቀናት በኋላ የሚቀርብ ቅሬታ /ቤታችን የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን።

15. የግንባታ ቁሳቁስ ግዥን በራሱ ትራንስፖርት //አስ/ገንዘብ መምሪያ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።

16. ለተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ ጎን/ከተ/አስ/ ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 126 03 06 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።

17. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

P.O.box-192 Tele- 0581-26-03-06

 

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ

Save Tender