በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለቀልጦ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ኮሚኒቲ ፋርማሲ ብቁ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ የግንባታ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለቀልጦ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ኮሚኒቲ ፋርማሲ ብቁ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለግንባታው የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል በምስ/አዘ/በር/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በመምጣት ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ መግዛት ትችላላችሁ።
በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች GC/BC-6 እና ከዛ በላይ የሆኑ
1. ተጫራቾች በዘርፉ ያላቸው የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ መቅታዊ የግብር ክፍያ ማረጋገጫ፣ የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ በአቅራቢዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የሚገልጽ ማስረጃና ሌሎች ሰነዶችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 80,000 (ሰማንያ ሺህ) ብር በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በCPO ምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም አሰርተው ለዚህ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በታሸገ ፖስታ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ ማስገባት አለባቸው። ዘግይቶ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
3. ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዶችን ለእያንዳቸው አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ የጨረታ ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ ህጋዊ ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሽገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው በ15ኛው ቀን በ8:00 ሰዓት ታሽጎ በዛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሠው አድራሻ ይከፈታል።
6. የግንባታው ሳይት (ቦታ) በምስ/አዘ/በ/ወረዳ በቂልጦ 01 ውስጥ ነው።
7. በተጫራቾች ተሞልተው የሚቀርቡ ፋይናንሻል ዋጋዎች እና የግንባታ ስራው ቴክኒካል የመወዳደሪያ ሀሳብ ደጋፊ ሰነዶች በግልጽና በጥራት የሚታዩና ስርዝ ወይም ድልዝ ያልሆኑ መሆን አለባቸው።
8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. የወረዳው ከተማ (ቂልጦ) ከአዲስ አበባ ርቀቱ 221 ኪሎ ሜትር ሲሆን 176 ኪሎ ሜትር አስፓልት እና 45 ኪሎ ሜትር ፒስታ መንገድ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 27 17 59 14 /09 33 62 02 20
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የፋይናንስ ጽ/ቤት
