Tender Detail

Tender Details

  • Company በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address የካቲት 12 ሆስፒታል ጀርባ በሚገኘው ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መንገድ ይዞ ከኢትዮጵያ ዓይነ ስውራን ማኅበር ፊት ለፊት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0111262899
  • Website
  • Deadline20 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2026-02-20 00:00:00
  • Categories Vehicles Rent , Cleaning And Janitorial Equipment , Labour Outsourcing Services

በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 6 አስተዳደር ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በ2ኛ ዙር ጨረታ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የፅዳት እቃዎች፣ የመኪና ኪራይ፣ የጉልበት/የጭነት አገልግሎት በ2ኛው ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድረን መግዛትና ማሠራት እንፈልጋለን።


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር:-02/2018

 

በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 6 አስተዳደር /ቤት 2018 በጀት ዓመት 2 ዙር ጨረታ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የፅዳት እቃዎች፣ የመኪና ኪራይ፣ የጉልበት/የጭነት አገልግሎት 2ኛው ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድረን መግዛትና ማሠራት እንፈልጋለን።

በዚህ መሠረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች-

1.     በዘርፉ አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን ነበር፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው።

2.     የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣

3.     ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ፋይናንስ /ቤት መውሰድ ይችላሉ።

4.     በተጨማሪ ተጫራቾች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

5.     በጨረታው ላይ ያወጣናቸውን እቃዎች በሙሉ አርጅናል እና ጥራቱን የጠበቁ ሆነው ማቅረብ የሚችሉ

6.     ተጫራቾች የጨረታ ፖስታ በሚያስገቡበት ጊዜ ለተወዳደሩበት እቃ ሳምፕል የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል።

7.     ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎችን በራሳቸው ትራንስፖርት /ቤቱ ድረስ ማምጣት የሚችሉ።

8.     ተጫራቾች በገዙት ሰነድ ብቻ የሚወዳደሩበትን ቫት በመጨመርና በእያንዳንዱ ገጽ ፊርማና የድርጅቱ ማህተም በማኖር በታሸገ ኢንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በተጠቀሰው ቢሮ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።

9.     የጨረታው ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ሎት 10,000 /አስር ሺ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ C.PU ብቻ ማቅረብ አለባቸው።

10. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸው እቃዎች አጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከጽ/ቤቱ ጋር የግዢ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርበታል።

11. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 11ኛው የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ የጨረታው አከፋፈት ላይ ለመገኘት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን /11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 430 ሰዓት በወረዳው አስተዳደር አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።

12./ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ተጫራቾች ለሳንኘል ለናሙና ማቅረቢያ የሚያገለግላቸውን በተጫራቹ ድርጅት ቅጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

 

አድራሻ፡- የካቲት 12 ሆስፒታል ጀርባ በሚገኘው ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መንገድ ይዞ ከኢትዮጵያ ዓይነ ስውራን ማኅበር ፊት ለፊት በሚገኘው በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር

ስልክ ቁጥር:- 0111262899/0111580697

 

በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 አስተዳደር ፋይናንስ /ቤት

Save Tender