የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የ2018/2019 ዓ.ም የሠራተኞች የአደጋ መከላከያ እና የደንብ ልብስ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ዝርዝር መሰረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢ.ግ.ሥ.ኮ/ብግጨ/8/2018
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የ2018/2019 ዓ.ም የሠራተኞች የአደጋ መከላከያ እና የደንብ ልብስ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ዝርዝር መሰረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር ለመክፈላችሁ ማስረጃ፡ የቫት ተመዝጋቢ ቲን እና በEGP የአቅራቢዎች ሊስት የተመዘገበ ስለመሆኑ ማስረጃ መቅረብ ይኖርበታል። እንዲሁም ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ በሚገኘው ፋፋ የምግብ አ.ማ ጀርባ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ የጠቅላላውን ብር 2% በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ (Unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። የጨረታ ዋጋ ለ60 (ስልሳ) ቀናት የጸና መሆን ይኖርበታል። ጨረታው የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ስነሥርዓት ይከናወናል ።
ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
ስልክ፡ +251911984467 ወይም +25149632090
ፋክስ 0114-421312
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
