Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Agriculture Bureau (የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ)
  • Address ባሕር ዳር : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: +251583207115
  • Website
  • Deadline24 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • opening date2026-02-24 00:00:00
  • Categories Gardening And Landscaping , Plastic Raw Materials And Products

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ ለተፈጥሮ ሀብት መሬት አጠቃቀም ዳይሬክቶሬት አገልግሎት የሚውል ሎት 01 የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ ባለ 10፣ ሎነ 02 የእጅ ጋሪ እና ሎት ዐ3 የውሃ ማጠጫ ጆርዲን ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።


በድጋሚ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ ለተፈጥሮ ሀብት መሬት አጠቃቀም ዳይሬክቶሬት አገልግሎት የሚውል ሎት 01 የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ ባለ 10 ሎነ 02 የእጅ ጋሪ እና ሎት 03 የውሃ ማጠጫ ጆርዲን ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

1.     በዘርፉ የተሰማሩ እና በዘመኑ ስለመታደሱ የሚገልጽ እና ግብር የከፈሉበትን ሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።

2.     የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤

3.     የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

4.     ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ. 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከአርጅናሉ ጋር በማገናዘብ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው

5.     የሚገዙ የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ ጆርዲን እና የዕጅ ጋሪ ግዥ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ እና መቅረብ ያለባቸው አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።

6.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 14 ማግኘት ይችላሉ፡፡

7.     ተጫራ ለሚወዳደሩበት ብር ጠቅላላ የዕቃ የግንባታ ወይም የአገልግሎት ዋጋ ብር በቁርጥ ዕለት 01 ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እንዲሁም ለሎት 02 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ሎት 03 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) እና በቅድመ ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባን ዋስትና (Unconditonal Bank Guarantee) ብቻ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ የመወዳደሪያ/ ሃሳቡን የቴክኒካል ሰነድ ዋና እና ቅጅ ለየብቻው እና የፋይናሽያል ሰነዱን እና የጨረታ ማስከበሪያውን በአንድ ዋና እና ቅጅ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግብርና ቢሮ ጊቢ ቢሮ ቁጥር 025 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ለተጠየቁት ግዥዎች ናሙናቸውን ከቴክኒካል ሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው

8.     ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግብርና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 16 ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 400 ታሽጎ 430 ይከፈታል።

9.     /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 25 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 2205849/0583208095/ በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

11. ተጫራቾች ያለምንም ስርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ይህ ካልሆነ ሰነዱ ተቀባይነት ላይኖረው ይቻላል፡፡ ባጋጣሚ የተሰረዘም ከሆነ የሞላው ድርጅት ፊርማ መኖር አለበት፡፡

12. በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ

Save Tender